እንደ ፡ ኢየሱስ (Ende Eyesus) - በረከት ፡ ለማ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
በረከት ፡ ለማ
(Bereket Lemma)

፩
(1)

አልበም
(1)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፪ (2)

ርዝመት (Len.): 6:50
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ፡ ለማ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Lemma)

አንተ ኖረህ በዚህች ምድር ላይ

ምሳሌ ሆንከኝ እሩቅ እንዳላይ

እታች ወርደህ እግር እንዳጠብክ

ለኔም ይቅለለኝ ወርዶ መታዘዝ
 

ይኸውና ወዳጄ ሰውነቴ ይኸውና ወዳጄ ማንነቴ (እኔነቴ)

ይኸውና ሰጠሁህ መንፍስ ቅዱስ ይኸውና አድርገኝ እንደ ኢየሱስ


የዋህ አድርገኝ በልቡ ትሁት /እንደ ኢየሱስ

እጀ ጠባቡን ቢቀሙት ካባውን/ዬን ሚሰጥ

ክፉውን በክፉ የማይመልስ

ሚጠሉትን ከነፍሱ የሚወድ

 
በዚህች ምድር ለአንድ ነገር ሮጣለሁ

የኢየሱሴን ፍለጋውን እከተላለሁ

በዚህች ምድር አንድ ነገር እመኛለሁ

መምህሬን እንድመስለው እሻለሁ


ትጉ አድርገኝ ፀሎት ማይታክት

ብርቱ አድርገኝ ሀጢያት ሚፀየፍ

ሚሰራ እስኪመስል ኢየሱስን

በሞቱ እንኳን በመሰልኩት የሚል


ይሄን መንገድ ይሄን ሩጫ እሮጠዋለሁ

የኢየሱስን ፍለጋውን እከተላለሁ

ያግዘኛል ይረዳኛል መንፈስ ቅዱስ

ይሰራኛል እስክመስል እንደ ኢየሱስ