From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
አውታሩ ፡ ከበደ (Awtaru Kebede)
|
|
|
|
፯ (7)
|
አልበም (እረፍት)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
| ቁጥር (Track):
|
፪ (2)
|
| ርዝመት (Len.):
|
5:05
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች (Albums by Awtaru Kebede)
|
|
|
በመንፈስህ ፡ ክብር ፡ ነክረህ ፡ አረስርሰኸኝ
ምንም ፡ ነገር ፡ እንዳይጎል ፡ አርገኸኝ
ደስታዬ ፡ ፍፁም ፡ ነው ፡ እንከን ፡ የሌለው
አንተን ፡ ብቻ ፡ ብዬኮ ፡ ቀረው
ኢየሱስ ፡ የሁሉ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
የሁሉ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የሁሉ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
ኢየሱስ ፡ የሁሉ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
የሁሉ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የኔኮ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
ትልቅ ፡ ቢሆን ፡ ትንሽ ፡ ደሃ ፡ ባለጠጋ
ፍቅርን ፡ ያገኛል ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ሲጠጋ (2x)
የማይጠፋ ፡ እርስት ፡ እንከን ፡ የሌለው
ህያው ፡ ተስፋ ፡ አለኝ ፡ እሱም ፡ ጌታ ፡ ነው
ያስታውቅብኛል ፡ እንደ ፡ ተጋባብኝ
ያንተ ፡ መንፈስ ፡ እንደ ፡ ረበበብኝ
በጨለማው ፡ አለም ፡ ሀዘን ፡ በሞላበት
በኔ ፡ ቤት ፡ ግን ፡ መዝሙር ፡ ፈለቀበት
ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ለኔ
ከሁሉ ፡ በላይ (2x)
የማይጠፋ ፡ እርስት ፡ እንከን ፡ የሌለው
ህያው ፡ ተስፋ ፡ አለኝ ፡ እሱም ፡ ጌታ ፡ ነው
|