የሕይወት ፡ ውኃ (Yehiwot Wiha) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

፮
(6)

አልበም
(፮)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፮ (6)

ርዝመት (Len.): 5:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

የእኔ ፡ ሙግት ፡ የእኔ ፡ ክርክር
ማንነቱን ፡ ሳልውቀው ፡ ነበር
የሕይወቴ ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ እንዳለ
ያስተዋልኩት ፡ ዘግይቼ ፡ ነበር

ጉዴን ፡ ውስጤን ፡ አውቆ ፡ የነገረኝ
ወደ ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ የመለሰኝ
ለካስ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ኢኢየሱስ ፡ ነው

ማን ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ
የሕይወት ፡ ውኃት ፡ ሰጣለህ
አንተ ፡ የምትሰጠውን ፡ የሚጠጣ
ዳግም ፡ እንዳይጠማው ፡ ታረካለህ
ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ነህ

ከያዕቆብ ፡ ጉድጓዶች ፡ የመነጨ ፡ ውሃ
ከቶ ፡ አያሻግርም ፡ የዓለምን ፡ በረሃ
አንተ ፡ ግን ፡ ኢኢየሱስ ፡ የምትሰጠው
ለዘላለም ፡ ሕይወት ፡ የሚያዘልቅ ፡ ነው
የዘላለም ፡ ነው

ማን ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ
የሕይወት ፡ ውኃት ፡ ሰጣለህ
አንተ ፡ የምትሰጠውን ፡ የሚጠጣ
ዳግም ፡ እንዳይጠማው ፡ ታረካለህ
ኢየሱስ ፡ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ነህ

ከሰማይ ፡ ወረደ ፡ የሕይወት ፡ እንጀራ
ዘላለም ፡ እንድኖር ፡ ከእርሱ ፡ ስበላ
ወዶ ፡ በፈቃዱ ፡ ራሱን ፡ አቀረበ
ደግ ፡ ቸር ፡ ጌታዬ ፡ ለነፍሴ ፡ ያሰበ
ለነፍሴ ፡ ያሰበ

ከእንግዲህ ፡ ከአንተ ፡ ወደት ፡ እሄዳለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት
የሕይወት ፡ ውኃ ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት
እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት
ከእንግዲህማ ፡ ከአንተ ፡ ወደት ፡ እሄዳለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት
የሕይወት ፡ ውኃ ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት
እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መሆንህን ፡ አውቄያለሁ
ከአንተ ፡ ወዴት