በመንፈስህ ፡ እንጂ (Bemenfesih Enji) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

፮
(6)

አልበም
(፮)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 5:59
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት

በፊቴ ፡ የቆመው ፡ ታላቅ ፡ ተራራ
አታልፉም ፡ ብሎ ፡ የሚያስፈራራ
ተደላድሎልን ፡ የተሻገርነው
ጌታ ፡ ሆይ ፡ በኃይልህ ፡ ነው
ከእኛ ፡ ነው ፡ ብለን ፡ የምንቆጥረው
በዘመናችን ፡ እስቲ ፡ የቱን ፡ ነው
ሁሉንም ፡ መልካም ፡ አድርገሃልና
ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት

አንድ ፡ ሁለት ፡ ብለን ፡ ዘመን ፡ ቆጥረናል
ክፉና ፡ ደጉን ፡ ሁሉን ፡ አይተናል
ዛሬ ፡ ላይ ፡ ቆመን ፡ ስናስተውለው
የአንተ ፡ ፀጋ ፡ ብዙ ፡ ነው
ኧረ ፡ እንዴት ፡ ብለን ፡ ደረስን ፡ እዚህጋ
መስሎን ፡ ነበር ፡ ሌቱ ፡ የማይነጋ
ማይቻለውን ፡ ላስቻልከን ፡ ጌታ
ይሁንልህ ፡ ዕልልታ

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት

የሄድንባቸው ፡ ረጅም ፡ መንገዶች ፡
ያለፍንባቸው ፡ እነዚያ ፡ ቀኖች
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ ነውና
ይሁንልህ ፡ ምሥጋና
በሕይወት ፡ እንድንኖር ፡ ምክንያት ፡ የሆነን
ከብዙ ፡ ጉዳት ፡ ጥፋት ፡ ያዳነን
የአንተ ፡ ብርቱ ፡ ክንድ ፡ ነውና ፡
ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና ፡

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት

በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በጉልበት
በመንፈስ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በዕውቀት