From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
|
|
፮ (6)
|
አልበም (፮)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
| ቁጥር (Track):
|
፲ ፩ (11)
|
| ርዝመት (Len.):
|
5:01
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
|
በዓለቱ ፡ ላይ ፡ የቆመ ፡ ቤት ፡ አለኝ
መሠረቱ ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ የጸና
በቀላሉ ፡ የማይገፋ ፡ የማይወድቅ ፡ በጊዜያዊ ፡ ፈተና
ቢጐርፍም ፡ ጐርፉ ፡ በላዬ ፡ ቢነፍስብኝም ፡ ነፋሱ
አንድ ፡ ነገት ፡ ግን ፡ ገብቶኛል ፡ አይችልም ፡ ሊለየኝ ፡ ከእርሱ
ቢጐርፍም ፡ ጐርፉ ፡ በላዬ ፡ ቢነፍስብኝም ፡ ነፋሱ
አንድ ፡ ነገት ፡ ግን ፡ አውቃለሁ ፡ አይችልም ፡ ሊለየኝ ፡ ከእርሱ
አለቴ ፡ መሠረቴ
ኢየሱስ ፡ ሕይወቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ ፡
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ
ክርስቶስ ፡ ሕይወቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ ፡
ጌታ ፡ የእግዚአሔር ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
ያመንኩትን ፡ ማን ፡ እንደሆን ፡ አውቃለሁ
ተፈትኖ ፡ አልፏል ፡ በመከራ
በድካሜ ፡ ከቶ ፡ ማይፈርድብኝ
ይልቅ ፡ ለእኔ ፡ የሚያስብ ፡ ነው ፡ ሚራራ
ሞትስ ፡ ቢሆን ፡ ወይንስ ፡ ሕይወት
ከፍታ ፡ ቢሆን ፡ ዝቅታ
ይህንን ፡ ተረድቻለሁ ፡ አይችል ፡ ሊለየኝ ፡ ከጌታ
ሞትስ ፡ ቢሆን ፡ ወይንስ ፡ ሕይወት
ከፍታ ፡ ቢሆን ፡ ዝቅታ
ይህንን ፡ ተረድቻለሁ ፡ አይችል ፡ ሊለየኝ ፡ ከጌታ
አለቴ ፡ መሠረቴ
ኢየሱስ ፡ ሕይወቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ ፡
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ
ክርስቶስ ፡ ሕይወቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ ፡
ጌታ ፡ የእግዚአሔር ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ ፡ በጌታዬ
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ ፡ በቃሉ ፡ ላይ
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ
አልነዋወጥም ፡ ሰድጃለሁ ፡ ስሬን
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ
ንፋስ ፡ ዓይነቅለኝም ፡ ሰድጃለሁ ፡ ስሬን
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ ፡ በጌታዬ
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ ፡ በቃሉ ፡ ላይ
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ
አልነዋወጥም ፡ ሰድጃለሁ ፡ ስሬን
ጸንቶ ፡ ቆሟል ፡ እግሬ
ንፋስ ፡ ዓይነቅለኝም ፡ ሰድጃለሁ ፡ ስሬን
አለቴ ፡ መሠረቴ
ኢየሱስ ፡ ሕይወቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ ፡
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ
ክርስቶስ ፡ ሕይወቴ
አለቴ ፡ መሠረቴ ፡
ጌታ ፡ የእግዚአሔር ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ ጉልበቴ
|