Azeb Hailu/Single

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

|ዘማሪ=አዜብ ፡ ሐይሉ አዝማች ተራራው ፡ ግዙፍ ፡ ቢመስል ለእኔ ፡ እንጂ ፡ ለአንተ ፡ አይደለም በፊትህ ፡ ከባድ ፡ የሚሆን የማትችለው ፡ አንድ ፡ እንኳን ፡ የለም እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ኃያል ፡ ነህ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ቀላል ፡ ነው ስታዝዘው ፡ የማይታዘዝህ ፡ ኤረ ፡ ከቶ ፡ የቱ ፡ ነው አምላኬ ፡ አንተ ፡ ኃያል ፡ ነህ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ቀላል ፡ ነው ስታዝዘው ፡ የማይታዘዝህ ፡ ኤረ ፡ ከቶ ፡ ምንድር ፡ ነው

፩) አንድ ፡ ነገር ፡ ሰማሁ ፡ እኔም ፡ አመንሁ ፡ እርሱን ኃይል ፡ የአንተ ፡ ብቻ ፡ የአንተ ፡ እንደሆነ ኃይል ፡ የአንተ ፡ ብቻ ፡ የአንተ ፡ እንደሆነ የሚጥል ፡ የሚያነሳ ፡ የሚገድል ፡ የሚያድን ኃይል ፡ የአንተ ፡ ብቻ ፡ የአንተ ፡ እንደሆነ ኃይል ፡ የአንተ ፡ ብቻ ፡ የአንተ ፡ እንደሆነ

አንተ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ፡ ከሆንህ ፡ የእኔ ፡ አባት ልረፍብህ ፡ እንጂ ፡ ልጠጋ ፡ በእምነት አንተ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ፡ ከሆንህ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ሁሉን ፡ ለአንተ ፡ ትቼ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ላምልክህ

ተራራው ፡ ግዙፍ...

፪) የሰው ፡ ልጅ ፡ ያየለ ፡ ቢመስለው ፡ በዕውቀቱ ከፀሐይዋ ፡ በታች ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ከፀሐይዋ ፡ በታች ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለዘላለም ፡ ያው ፡ ነህ ሥራህ ፡ ሁሉ ፡ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ የሆነልህ ሥራህ ፡ ሁሉ ፡ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ የሆነልህ

አንተ ፡ ብርቱ ፡ ጌታ ...

ተራራው ፡ ገዝፎ ፡ ቢታይ ለእኔ ፡ እንጂ ፡ ለአንተ ፡ አይደለም በፊትህ ፡ ከባድ ፡ የሚሆን የማትችለው ፡ አንድ ፡ እንኳን ፡ የለም እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ኃያል ፡ ነህ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ቀላል ፡ ነው ስታዝዘው ፡ የማይታዘዝህ ፡ ኤረ ፡ ከቶ ፡ የቱ ፡ ነው አምላኬ ፡ አንተ ፡ ኃያል ፡ ነህ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ቀላል ፡ ነው ስታዝዘው ፡ የማይታዘዝህ ፡ ኤረ ፡ ከቶ ፡ ምንድር ፡ ነው

ኤረ ፡ ለአምላኬ ፡ ይህቺ ፡ ምንድር ፡ ናት? በጣም ፡ ቀላል ፡ ናት ፡ በጣም ፡ ቀላል ፡ በጣም ፡ ቀላል ኤረ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይህቺ ፡ ምንድር ፡ ናት? በጣም ፡ ቀላል ፡ ናት ፡ በጣም ፡ ቀላል ፡ በጣም ፡ ቀላል

ቀላል ፡ ነው (፲፪)

ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አመልክሃለሁ ስለዚህ ፡ አምላኬ ፡ አከብርሃለሁ ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ አመልክሃለሁ ስለዚህ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ አመልክሃለሁ

አመልክሃለሁ (፰)