ማደሪያው (Maderiyaw) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

፮
(6)

አልበም
(፮)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

በልቤ ፡ አድሮ ፡ የነበረ ፡ ኮተታ ፡ ኮተት ፡ ቆሻሻው
ተጠርጐ ፡ ወጣ ፡ ለቀቀ ፡ ስፍራውን ፡ ለሚገባው
ታጠበ ፡ ጸዳ ፡ አማረ ፡ ተሸላለመ ፡ ለጌታ
ንጉሤን ፡ ሾምኩት ፡ በልቤ ፡ ሳመልከው ፡ በደስታ

ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ለክብሩ ፡ ለየኝ

ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ለክብሩ ፡ ለየኝ

ውዴ ፡ በበር ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ሲያንኳኳ ፡ ደጄን ፡ ሲመታ
የሕይወት ፡ እንጀራን ፡ ይዞ ፡ አዘጋጅሮልኝ ፡ ገበታ
ነፍሴን ፡ ሊያጠግባት ፡ ከፍቅሩ ፡ ዘልቆ ፡ ሲገባ ፡ ከቤቴ
ነገር ፡ ሁሉ ፡ እንዳልነበረ ፡ ተቀያየረ ፡ ሕይወቴ

ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ለክብሩ ፡ ለየኝ

ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ለክብሩ ፡ ለየኝ

ቃሉን ፡ ገለጠ ፡ ለነፍሴ ፡ የጌታ ፡ መንፈስ ፡ መምህሩ
ገብቶኛል ፡ ተረድቻለሁ ፡ ለካስ ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ነገሩ
ውዴ ፡ ሆኖኛል ፡ ለእኔ ፡ እኔም ፡ ለእርሱ ፡ ሆኛለሁ
ለሌላው ፡ እንዳልሆን ፡ ሆኜ ፡ በቃል ፡ ኪዳን ፡ ታስሬያለሁ

ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ለክብሩ ፡ ለየኝ

ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ማደሪያው ፡ መቅደሱ ፡ አደረገኝ
ለክብሩ ፡ ለየኝ