አልተሳሳትኩ (Altesasatku) - ካሮል ፡ ፈቃዱ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ካሮል ፡ ፈቃዱ
(Carol Fekadu)

፭
(5)

አልተሳሳትኩ
(Altesasatku)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፫ (3)

ጸሐፊ (Writer): ካሮል ፡ ፈቃዱ
(Carol FekaduProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሮል ፡ ፈቃዱ ፡ አልበሞች
(Albums by Carol Fekadu)

አንዳንድ ግዜ በህይወት ጎዳና ስፈተን ይከብድና
የማደርገው ሳጣ ግራ ስጋባ ምግቤ ሲሆን እንባ
ስጠራጠር መኖርህን ላፍታ ስል አለህ ወይ ጌታ
የትላንቱ እምነቴ ሲጠፋ የኪዳንህ ተስፋ/2

አለው ልጄ ብለህ
ደጋግፈህ አቁመህ
እጄን በእጅህ ይዘህ
አየው ታማኝ ሆነህ/2

ታማኝ ነህ በማለቴ/4

አልተሳሳትኩ አላጋነንኩ
አተረፍኩ እንጂ አልከሰርኩ/2

እምነቴ ጠፍቶ ሳልታመንብህ አየሁ ታማኝ ሆነህ
ከዛ ሸለቆ ከረመጥ አውጥተህ አየሁ ታማኝ ሆነህ
ከእጅህ በልቼ እንዳለረፍኩብህ አየሁ ታማኝ ሆነህ
ስንቴ ስሸሽህ አንተ ግን ታግሰህ አየሁ ታማኝ ሆነህ

እምነቴ ጠፍቶ ሳልታመንብህ አየሁ ታማኝ ሆነህ
ከዛ ሸለቆ ከረመጥ አውጥተህ አየሁ ታማኝ ሆነህ
ከእጅህ በልቼ እንዳለረፍኩብህ አየሁ ታማኝ ሆነህ
ስንቴ ስሸሽህ አንተ ግን ታገስከኝ አየሁ ታማኝ ሆነህ

አለው ልጄ ብለህ
ደጋግፈህ አቁመህ
እጄን በእጅህ ይዘህ
አየው ታማኝ ሆነህ/2

ታማኝ ነህ በማለቴ/4

አልተሳሳትኩ አላጋነንኩ
አተረፍኩ እንጂ አልከሰርኩ

ታማኝ ነህ በማለቴ/4

አልተሳሳትኩ አላጋነንኩ
አተረፍኩ እንጂ አልከሰርኩ