ህልውናህ (Hulwunah) - ካሮል ፡ ፈቃዱ

ካሮል ፡ ፈቃዱ
(Carol Fekadu)

፭
(5)

አልተሳሳትኩ
(Altesasatku)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፮ (6)

ጸሐፊ (Writer): ካሮል ፡ ፈቃዱ
(Carol FekaduProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሮል ፡ ፈቃዱ ፡ አልበሞች
(Albums by Carol Fekadu)

የምለው ሌላ የለኝ ቃላቶች አጥረውኛል
ቋንቋዬ ባይገልፅልህ ልቤ በፊትህ ይፈሳል/2

በመገኘትህ ሆኜ ይምልው ጠፍቶብኛል
በህልውናህ ሆኜ ቃላቶቼ ቀልጠዋል

ልምላሜ ነው ሁልጊዜ ካንተ ጋር ሆኜ
መድረቅ አልችልም ይፈልቃል ምንጩ ከውስጤ
በህልውናህ ማደርያ ውስጥ ተዘልዬ
ሰማያዊ ጠል ይፈሳል ዘይት በላዬ

ማይለመድ ነው ሁሌም ህልውናህ ህልውናህ/4

ሸክሜን ይዤ ስመጣ ፊትህ ስደፋ
አይታወቀኝ ከላዬ ቀልጦ ሲጠፋ
አይሰለቸኝም መቆየት መዋል ካንተጋ
ማይለመድ ነው ጠረንህ ያንተ መዓዛ

ህመሜን ይዤ ስመጣ ፊትህ ስደፋ
አይታወቀኝ ከላዬ ቀልጦ ሲጠፋ
አይሰለቸኝም መቆየት መዋል ካንተጋ
ማይለመድ ነው ጠረንህ ያንተ መዓዛ

ማይለመድ ነው ሁሌ ህልውናህ ህልውናህ/2
ማይሰለች ነው ሁሌ ህልውናህ ህልውናህ/2
ማይጠገብ ነው ሁሌ ህልውናህ ህልውናህ/2

ህልውናህ ጌታ ህልውናህ/2
ህልውናህ አባ ህልውናህ/2
ህልውናህ ሁሌ ህልውናህ/2
ህልውናህ ለኔ ህልውናህ/2