ትወደኛለህ (Tiwedegnaleh) - ካሮል ፡ ፈቃዱ

ካሮል ፡ ፈቃዱ
(Carol Fekadu)

፭
(5)

አልተሳሳትኩ
(Altesasatku)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፪ (2)

ጸሐፊ (Writer): ካሮል ፡ ፈቃዱ
(Carol FekaduProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የካሮል ፡ ፈቃዱ ፡ አልበሞች
(Albums by Carol Fekadu)

ተገልጦ ተነቦ የማያልቀው
የፍቅርህ መዝገብ ሰፊ ነው/3
ፈልቆ ተቀድቶ የማይደርቀው
የመውደድህ ምንጩ ጥልቅ ነው/3

ትወደኛለህ/3 ይህን አውቃለው

መሊቅ ነው ማይለካ የመውደድህ ውቅያኖስ
ርዝመቱ ያለፈ ነው ከሃሳቤ አድማስ
ዘላለማዊ ነው ፍቅርህ ወረት የሌለው
እንዱሁ እንደወደድከኝ ይህንን አውቃለው

ትወደኛለህ/3 ይህን አውቃለው

ቋንቋዎች ተደባልቀው ቃላቶች ተጨፍልቀው
የልቤን የመውደዴን ብርታት ቢገልፁ ምነው
ገብቶኛል አውቄያለው ምሳሌ እንደማይገልፀው
ዝም ብዬ ቀጥላለው መውደዴን ወደዋለው

እወደዋለው/3 አንተን መውደዴን
እጨምረዋለው/3 አንተን መውደዴን
እወደዋለው/3 አንተን መውደዴን
እጨምረዋለው/3 አንተን መውደዴን

እወደዋለው/6 አንተን መውደዴን