፪ኛ ፡ የጴጥሮስ ፡ መልእክት - ምዕራፍ ፬ (1st Peter - Chapter 4)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search


፩፡ ክርስቶስም ፡ በሥጋ ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ መከራን ፡ ስለተቀበለ ፥ ከእንግዲህ ፡ ወዲህ ፡ በሥጋ ፡ ልትኖሩ ፡ በቀረላችሁ ፡ ዘመን ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ እንጂ ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ምኞት ፡ እንዳትኖሩ ፥ እናንተ ፡ ደግሞ ፡ ያን ፡ አሳብ ፡ እንደ ፡ ዕቃ ፡ ጦር ፡ አድርጋችሁ ፡ ያዙት ፥ በሥጋ ፡ መከራን ፡ የተቀበለ ፡ ኃጢአትን ፡ ትቶአልና። ፪፡ የአሕዛብን ፡ ፈቃድ ፡ ያደረጋችሁበት ፡ በመዳራትና ፡ በሥጋ ፡ ምኞትም ፡ በስካርም ፡ በዘፈንም ፡ ያለ ፡ ልክም ፡ በመጠጣት ፡ ነውርም ፡ ባለበት ፡ በጣዖት ፡ ማምለክ ፡ የተመላለሳችሁበት ፡ ያለፈው ፡ ዘመን ፡ ይበቃልና። ፫፡ በዚህም ፡ ነገር ፡ ወደዚያ ፡ መዳራት ፡ ብዛት ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ ስለማትሮጡ ፡ እየተሳደቡ ፡ ይደነቃሉ ፤ ፬፡ ግን ፡ እነርሱ ፡ በሕያዋንና ፡ በሙታን ፡ ላይ ፡ ሊፈርድ ፡ ለተዘጋጀው ፡ መልስ ፡ ይሰጣሉ። ፭፡ እንደሰዎች ፡ በሥጋ ፡ እንዲፈረድባቸው ፡ በመንፈስ ፡ ግን ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዲኖሩ ፡ ስለዚህ ፡ ምክንያት ፡ ወንጌል ፡ ለሙታን ፡ ደግሞ ፡ ተሰብኮላቸው ፡ ነበርና። ፮፡ ዳሩ ፡ ግን ፡ የነገር ፡ ሁሉ ፡ መጨረሻ ፡ ቀርቦአል። እንግዲህ ፡ እንደ ፡ ባለ ፡ አእምሮ ፡ አስቡ ፥ ፯፡ ትጸልዩም ፡ ዘንድ ፡ በመጠን ፡ ኑሩ ፤ ፍቅር ፡ የኃጢአትን ፡ ብዛት ፡ ይሸፍናልና ፡ ከሁሉ ፡ በፊት ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ አጥብቃችሁ ፡ ተዋደዱ። ፰፡ ያለ ፡ ማንጐራጐር ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ እንግድነትን ፡ ተቀባበሉ ፤ ፱፡ ልዩ ፡ ልዩን ፡ የእግዚአብሔርን ፡ ጸጋ ፡ ደጋግ ፡ መጋቢዎች ፡ እንደ ፡ መሆናችሁ ፥ እያንዳንዳችሁ ፡ የጸጋን ፡ ስጦታ ፡ እንደ ፡ ተቀበላችሁ ፡ መጠን ፡ በዚያው ፡ ጸጋ ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ አገልግሉ ፤ ፲፡ ማንም ፡ ሰው ፡ የሚናገር ፡ ቢሆን ፥ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ይናገር ፤ የሚያገለግልም ፡ ቢሆን ፥ እግዚአብሔር ፡ በሚሰጠኝ ፡ ኃይል ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ያገልግል ፤ ክብርና ፡ ሥልጣን ፡ እስከ ፡ ዘላለም ፡ ድረስ ፡ ለእርሱ ፡ በሚሆነው ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ በኩል ፡ እግዚአብሔር ፡ በነገር ፡ ሁሉ ፡ ይከብር ፡ ዘንድ ፤ አሜን። ፲፩፡ ወዳጆች ፡ ሆይ ፥ በእናንተ ፡ መካከል ፡ እንደ ፡ እሳት ፡ ሊፈትናችሁ ፡ ስለሚሆነው ፡ መከራ ፡ ድንቅ ፡ ነገር ፡ እንደ ፡ መጣባችሁ ፡ አትደነቁ ፤ ፲፪፡ ነገር ፡ ግን ፡ ክብሩ ፡ ሲገለጥ ፡ ደግሞ ፡ ሐሤት ፡ እያደረጋችሁ ፡ ደስ ፡ እንዲላችሁ ፥ በክርስቶስ ፡ መከራ ፡ በምትካፈሉበት ፡ ልክ ፡ ደስ ፡ ይበላችሁ። ፲፫፡ ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም ፡ ብትነቀፉ ፡ የክብር ፡ መንፈስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ በእናንተ ፡ ላይ ፡ ያርፋልና ፡ ብፁዓን ፡ ናችሁ። ፲፬፡ ከእናንተ ፡ ማንም ፡ ነፍሰ ፡ ገዳይ ፡ ወይም ፡ ሌባ ፡ ወይም ፡ ክፉ ፡ አድራጊ ፡ እንደሚሆን ፡ ወይም ፡ በሌሎች ፡ ጒዳይ ፡ እንደሚገባ ፡ ሆኖ ፡ መከራን ፡ አይቀበል ፤ ፲፭፡ ክርስቲያን ፡ እንደሚሆን ፡ ግን ፡ መከራን ፡ ቢቀበል ፡ ስለዚህ ፡ ስም ፡ እግዚአብሔርን ፡ ያመስግን ፡ እንጂ ፡ አይፈር። ፲፮፡ ፍርድ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ ተነሥቶ ፡ የሚጀመርበት ፡ ጊዜ ፡ ደርሶአልና ፤ አስቀድሞም ፡ በእኛ ፡ የሚጀመር ፡ ከሆነ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ወንጌል ፡ የማይታዘዙ ፡ መጨረሻቸው ፡ ምን ፡ ይሆን ? ፲፯፡ ጻድቅም ፡ በጭንቅ ፡ የሚድን ፡ ከሆነ ፡ ዓመፀኛውና ፡ ኃጢአተኛው ፡ ወዴት ፡ ይታይ ፡ ዘንድ ፡ አለው ? ፲፰፡ ስለዚህ ፡ ደግሞ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ መከራን ፡ የሚቀበሉ ፥ መልካምን ፡ እያደረጉ ፡ ነፍሳቸውን ፡ ለታመነ ፡ ፈጣሪ ፡ አደራ ፡ ይስጡ።