፪ኛ ፡ የጴጥሮስ ፡ መልእክት - ምዕራፍ ፭ (1st Peter - Chapter 5)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search


፩፡ እንግዲህ ፡ እኔ ፥ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ ሽማግሌ ፡ የክርስቶስም ፡ መከራ ፡ ምስክር ፡ ደግሞም ፡ ሊገለጥ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ተካፋይ ፡ የሆንሁ ፥ በመካከላቸው ፡ ያሉትን ፡ ሽማግሌዎች ፡ እመክራቸዋለሁ ፤ ፪፡ በእናንተ ፡ ዘንድ ፡ ያለውን ፡ የእግዚአብሔርን ፡ መንጋ ፡ ጠብቁ ፤ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ በውድ ፡ እንጂ ፡ በግድ ፡ ሳይሆን ፥ በበጎ ፡ ፈቃድ ፡ እንጂ ፡ መጥፎውን ፡ ረብ ፡ በመመኘት ፡ ሳይሆን ፡ ጐብኙት ፤ ፫፡ ለመንጋው ፡ ምሳሌ ፡ ሁኑ ፡ እንጂ ፡ ማኅበሮቻችሁን ፡ በኃይል ፡ አትግዙ ፤ ፬፡ የእረኞችም ፡ አለቃ ፡ በሚገለጥበት ፡ ጊዜ ፡ የማያልፈውን ፡ የክብርን ፡ አክሊል ፡ ትቀበላላችሁ። ፭፡ እንዲሁም ፥ ጐበዞች ፡ ሆይ ፥ ለሽማግሌዎች ፡ ተገዙ ፤ ሁላችሁም ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ እየተዋረዳችሁ ፡ ትሕትናን ፡ እንደ ፡ ልብስ ፡ ታጠቁ ፥ እግዚአብሔር ፡ ትዕቢተኞችን ፡ ይቃወማልና ፥ ለትሑታን ፡ ግን ፡ ጸጋን ፡ ይሰጣል። ፮፡ እንግዲህ ፡ በጊዜው ፡ ከፍ ፡ እንዲያደርጋችሁ ፡ ከኃይለኛው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ በታች ፡ ራሳችሁን ፡ አዋርዱ ፤ ፯፡ እርሱ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ ያስባልና ፡ የሚያስጨንቃችሁን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ጣሉት። ፰፡ በመጠን ፡ ኑሩ ፡ ንቁም ፥ ባላጋራችሁ ፡ ዲያብሎስ ፡ የሚውጠውን ፡ ፈልጎ ፡ እንደሚያገሣ ፡ አንበሳ ፡ ይዞራልና ፤ ፱፡ በዓለም ፡ ያሉት ፡ ወንድሞቻችሁ ፡ ያን ፡ መከራ ፡ በሙሉ ፡ እንዲቀበሉ ፡ እያወቃችሁ ፡ በእምነት ፡ ጸንታችሁ ፡ ተቃወሙት። ፲፡ በክርስቶስ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ ዘላለም ፡ ክብሩ ፡ የጠራችሁ ፡ የጸጋ ፡ ሁሉ ፡ አምላክ ፡ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ መከራን ፡ ከተቀበላችሁ ፡ በኋላ ፡ ራሱ ፡ ፍጹማን ፡ ያደርጋችኋል ፡ ያጸናችሁምል ፡ ያበረታችሁማል። ፲፩፡ ለእርሱ ፡ ክብርና ፡ ኃይል ፡ እስከዘላለም ፡ ድረስ ፡ ይሁን ፤ አሜን። ፲፪፡ እየመከርኋችሁና ፡ የምትቆሙባት ፡ ጸጋ ፡ እውነትኛ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ጸጋ ፡ እንድትሆን ፡ እየመሰከርሁላችሁ ፥ የታመነ ፡ ወንድም ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ በቈጠርሁት ፡ በስልዋኖስ ፡ እጅ ፡ በአጭሩ ፡ ጽፌላችኋለሁ። ፲፫፡ ከእናንተ ፡ ጋር ፡ ተመርጣ ፡ በባቢሎን ፡ ያለች ፡ ቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ልጄም ፡ ማርቆስ ፡ ሰላምታ ፡ ያቀርቡላችኋል። ፲፬፡ በፍቅር ፡ አሳሳም ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ ሰላምታ ፡ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ፡ ላላችሁ ፡ ለሁላችሁ ፡ ሰላም ፡ ይሁን። አሜን።