አምላኬ (Amlakie) - ብዙ ፡ ሙሉጌታ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ብዙ ፡ ሙሉጌታ
(Bezu Mulugeta)

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(1)

ቁጥር (Track):

፬ (4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ አልበሞች
(Albums by Bezu Mulugeta)

አምላኬ(4)
ከለላ መሸሸጊያዬ
የዘላለም መኖሪያዬ

መስኪኑን ማን አይቶት ነበር
አጥበኸው በእርሱ ስትከብር
ፍቅርህ በዝቷል በሕይወቴ
ክበርልኝ መድሀኒቴ።
የውስጤን አንተ ተረዳህ
ድካሜን መቼ ዘነጋህ
እንዳልወድቅ በረግረጉ ላይ
ተዋረድክ መጣህ ከሰማይ።

አምላኬ(4)
ከለላ መሸሸጊያዬ
የዘላለም መኖሪያዬ

ውጣ ብለህ ከሃገሬ
ከዘመድ ከአዝማዶቼ
ስትለየኝ ወደ ምድርህ
አልራቀብኝ አንዴም እጅህ
የሁሉ አባት አደረከኝ
በበረከትህ ባረከኝ
አርስቴ ባንተ አማረልኝ
ኤልሻዳዩ ክበርልኝ።

አምላኬ(4)
ከለላ መሸሸጊያዬ
የዘላለም መኖሪያዬ

እንደምትወደኝ አውቃለሁ
ብትዘገይም እነሳለሁ
ክብርህን ልትገልጥ ስትፈልግ
ሰው ባለህ አንተ አታደርግ