አምልኮዬ (Amelkoyie) - ብዙ ፡ ሙሉጌታ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ብዙ ፡ ሙሉጌታ
(Bezu Mulugeta)

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(special)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:10
ጸሐፊ (Writer): በረከት ተረፈ
(Bereket TerefeProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የብዙ ፡ ሙሉጌታ ፡ አልበሞች
(Albums by Bezu Mulugeta)

አምልኮዬ ይገባሃል

ላምልከው እያልኩኝ እወደዋለሁኝ
የመስቀሉን ሚስጥር ፍቅር እያየሁኝ፥
ውለታው ስለ እኔ እጅግ በዝቷልና
እኔም አበዛለው ለስሙ ምስጋና።

የተነሱበትን ጥሎ አዋረዳቸው
ስልጣኑን ቀምቶ ባዶ አደረጋቸው
እነማን በርትተው እግዚአብሔርን ሻሩ
እርሱ እኮ ይኖራል በነበረ ክብሩ።

ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(4)
ፍቅጄ አመልከዋለው ወድጄ እንብረከካለው
ልናገር ከምችለው በላይ ትልቅ ነው የክንዱ ስልጣን
ገብቶኛል እዘምራለው ስልጣኑ ከማንም በላይ ነው።

እንዴት ልናወጥ እንዴትስ ልፍራ
እያየው እክንዱን ስራ
ተደላድዬ ቆሚያለው
ሃያሉን ክንዱን ይዣለው
ሊሰራ እርሱ ሲነሳ
እያየው ሁሉም ይታዘዛል።

ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(4)

ሃያል ነን ጎበዝ ነን ያሉ
በእርሱ ላይ ብዙ ፎከሩ
ታገሰ ዘመን ሰጣቸው
ታበዪ ክንዱ አጠፋቸው
በዘመን በታሪክ የለም
ስልጣኑ ፍጹም አልተሻረም።

ስልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው(8)