Bezu Mulugeta/Kamlakachen Beqer Manew Amlak/Kamlakachen Beqer
ዘማሪ ፡ ብዙ ፡ ሙሉጌታ ርዕስ ፡ ከአምላካችን ፡ በቀር ጸሐፊ ፡ ሙሴ
ካምላካችን ፡ በቀር ፡ ማነው ፡ አምላክ ከአለቱስ ፡ በቀር ፡ ማነው ፡ አለት እየሱስ ፡ እየሱስ ፡ የድል ፡ ጋሻ ለክፉቀን ፡ ሆነልን ፡ መሸሻ ጌታችንን እኛ ፡ እናምነዋለን አሸንፎ ፡ ባይናችን ፡ ስላየን እየሱስን ፡ እኛ ፡ እናምነዋለን አሸንፎ ፡ ባይናችን ፡ ስላየን።
ብዙዎች ፡ ተነሱ ፡ በእርሱ ፡ ላይ በስልጣን ፡ በሃይሉ ፡ በክብሩ ፡ ላይ አልጸኑም ፡ ወድቀዋል ፡ ተገርስሰው በሃያሉ ፡ ክንዱ ፡ ተመልሰው እኛም ፡ ታምነንበት ፡ በዚህ ፡ ጌታ እንዘላለን ፡ ዛሬ ፡ በደስታ።
ኦሆ ... እኔ ፡ ማመልከው
ኦሆ ... የምስግድለት
ኦሆ ... የምገዛለት
አምላኬ ፡ እግዚአብሄር ፡ ይሄ ፡ ነው።
አማልክቶች ፡ አሉ ፡ በመደር ፡ ላይ ዝናቸው ፡ ለጥቂት ፡ ገኖ ፡ ሚታይ አይጸኑም ፡ ይወድቃሉ ፡ በአንድ ፡ አፍታ ሲነሳ ፡ በሃይሉ ፡ ይሄ ፡ ጌታ ሲያሰግድ ፡ አየነው ፡ በአይናችን ሕዝቡን ፡ ያስከብራል ፡ አምላካችን።
አባቶቻችንም ፡ ተማምነውት ነብያት ፡ ሐዋርያት ፡ ስሙን ፡ ጠሩት ሰማና ፡ ተገኝቶ ፡ አሳረፋቸው በጠላት ፡ ፊት ፡ መፈራት ፡ ሆናቸው ጥንት ፡ በደንቅ ፡ የሰራው ፡ ይሄ ፡ ጌታ በዙፋኑ ፡ አለ ፡ ሰይረታ።
እንደ ፡ አምላካችን ፡ ማነው ፡ አለን
በስሙ ፡ በክንዱ ፡ እኛ ፡ ፎከርን
በመከራው ፡ ዘመን ፡ ተማመንነው
ይሰራል ፡ ጌታችን ፡ ሃይለኛ ፡ ነው
ለሁሉም ፡ ይሄን ፡ ክንዱን ፡ አሳያቸው
እየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ አሰኛቸው።