From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
|
|
፭ (5)
|
አልበም (፭)
|
| ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፱ (2017)
|
| ቁጥር (Track):
|
፰ (8)
|
| ርዝመት (Len.):
|
4:12
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
|
አላመልክም ፡ ሞቶ ፡ የቀረ ፡ የተነሳውን ፡ ነው ፡ እንጂ
እውነት ፡ ነው ፡ ሞቶ ፡ ነበር ፡ ግን ፡ ተነስቷል ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ
ገደልነው ፡ ብለው ፡ ቢያወሩ ፡ አኑረነዋል ፡ ከመቃብር
በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳ ፡ በትንሳኤው ፡ ታላቅ ፡ ክብር
ተነሳ ፡ ሞት ፡ ተሸነፈ ፡ ተነሳ ፡ ኃይል ፡ አጣ ፡ ከቶ
ተነሳ ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ ተነሳ ፡ መቼ ፡ በርትቶ
ተነሳ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ ፡ ተነሳ ፡ ወጣ ፡ ወደላይ
ተነሳ ፡ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ተነሳ ፡ ከብሯል ፡ በሰማይ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
በትንሳኤው ፡ ቀን ፡ ማለዳ ፡ ባዶ ፡ ነበር ፡ መቃብሩ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ እንደወጣ ፡ መላእክቱ ፡ መሰከሩ
ሃዋርያቱም ፡ አስታወሱ ፡ የተሰጣቸውን ፡ ተስፋ
ጊታቸው ፡ ሞቶ ፡ እንደማይቀር ፡ እንደ ፡ ሌሎች ፡ እንደማይጠፋ
ተነስቷል ፡ ሞት ፡ ተሸነፈ ፡ ተነስቷል ፡ ኃይል ፡ አጣ ፡ ከቶ
ተነስቷል ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ ተነስቷል ፡ መቼ ፡ በርትቶ
ተነስቷል ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አለ ፡ ተነስቷል ፡ ወጣ ፡ ወደላይ
ተነስቷል ፡ በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ተነስቷል ፡ ከብሯል ፡ በሰማይ
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
የትንሳኤው ፡ ምስክሮች ፡ አይተውታል ፡ በዓይናቸው
በመካከላቸው ፡ ቆሞ ፡ ሰላም ፡ ለእናንተ ፡ ሲላቸው
በእጆቻቸው ፡ ዳስሰዋል ፡ የችንካሩን ፡ ምልክት
በእርግጥም ፡ ያ ፡ ኢየሱስ ፡ የተነሳው ፡ ነው ፡ ከሞት ፡
ተነሳ ፡ እንደ ፡ ሌኡቹ ፡ ተነሳ ፡ አልቀረም ፡ በምድር
ተነሳ ፡ የእኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ተነሳ ፡ ወጥቷል ፡ በክብር
ተነሳ ፡ ይመርመር ፡ ይታይ ፡ ተነሳ ፡ ታሪክ ፡ ይጠና
ተነሳ ፡ እንደ ፡ ጌታችን ፡ ተነሳ ፡ ሌላ ፡ የለምና
ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱሴ
ቢጠብቁ ፡ ቢያስጠብቁ ፡ መቃብሩ ፡ ላይ ፡ አትመው ፡ ኦ
እነሳለሁ ፡ ብሎ ፡ እንዳለ ፡ እንዳይነሳ ፡ እናድርግ ፡ ብለው ፡ ኦ
እንኳን ፡ ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ቀርቶ ፡ አልቻለችውም ፡ ምድሪቱ ፡ ኦ
ሕያው ፡ ሆኖ ፡ አሸንፏል ፡ በቃ ፡ ይኸው ፡ ነው ፡ እውነቱ ፡ ኦ
|