Azeb Hailu/Bemejemeria Egziabhier/Eregnaye
እረኛ
|ስለበዛልኝ ፡ ምህረቱ ፡ ስለደገፈኝ ፡ ፀጋው
መቋጫ ፡ ከቶ ፡ አጣሁኝ ፡ ሳወራው ፡ ቢመሽ ፡ ቢነጋ
የመልካም ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ምንጭ ፡ የበጐ ፡ ነገር ፡ መገኛ
የሆነው ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ እረኛ (2x)
እረኛዬ ፡ የነፍሴ ፡ መሰማሪያ
እረኛዬ ፡ መዋያዬና ፡ ማደሪያ
እረኛዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መኖሪያ (፪)
አዝ
በምድር ፡ ላለው ፡ ህይወቴ ፡ ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ጀምሮ
መች ፡ ያልቃል ፡ የርሱ ፡ ቸርነት ፡ ተዘርዝሮና ፡ ተነግሮ
አምላኬ ፡ ለኔ ፡ ያረገው ፡ ባወራው ፡ ከቁጥር ፡ በዛ
ልዘምር ፡ እንጂ ፡ ሳልሰለች ፡ ሳልቆጥበው ፡ እንደ ፡ ዋዛ
እረኛዬ ፡ የነፍሴ ፡ መሰማሪያ
እረኛዬ ፡ መዋያዬና ፡ ማደሪያ
እረኛዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መኖሪያ (፪)
አዝ
ሃጥኡ ፡ ፀሃይን ፡ ሞቆ ፡ የአንተን ፡ ምስጋና ፡ ካወራ
ምህረትህን ፡ ያየሁ ፡ እኔ ፡ እኔማ ፡ እንዴት ፡ አላወራ
በልጅህ ፡ የአንተ ፡ ልጅ ፡ ሆኜ ፡ ገብቼ ፡ ደጅህ ፡ ተከፍቶልኝ
ያየሁት ፡ እና ፡ የቀመስኩት ፡ የምለው ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ አለኝ
እረኛዬ ፡ የነፍሴ ፡ መሰማሪያ
እረኛዬ ፡ መዋያዬና ፡ ማደሪያ
እረኛዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መኖሪያ (፪)
አዝ
ሙሉ ፡ ሆኖ ፡ እንደሚፈስ ፡ እንደ ፡ ውሀ ፡ ነው ፡ ሰላሜ
በክርስቶስ ፡ ባገኘሁት ፡ የህይወት ፡ ቃል ፡ ነው ፡ መለምለሜ
ከማይነጥፍ ፡ ከማይደርቀው ፡ የህይወት ፡ ምንጭ ፡ ተጠግቼ
የዚህን ፡ አለም ፡ በረሃ ፡ የድርቅ ፡ ወሬ ፡ መች ፡ ፈርቼ
እረኛዬ ፡ የነፍሴ ፡ መሰማሪያ
እረኛዬ ፡ መዋያዬና ፡ ማደሪያ
እረኛዬ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ መኖሪያ (፪)
አዝ