ሌሊቱ ፡ ነጋ (Lelitu Nega) - አውታሩ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አውታሩ ፡ ከበደ
(Awtaru Kebede)

፬
(4)

ሌሊቱ ፡ ነጋ
(Lelitu Nega)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2005)
ቁጥር (Track):

፪ (2)

ርዝመት (Len.): 7:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአውታሩ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች
(Albums by Awtaru Kebede)

ዘማሪ አውታሩ ከበደ
ርዕስ ያለኝ ይሄ ነው
አልበም ሌሊቱ ነጋ

አምልኬ አልጠግብ አልኩኝ ጌታዬ
አንግሼ አልጠግብ አልኩኝ ወዳጄ
አጣሁ አጣሁኝ አንተን የሚተካ
በምድር በሰማይ አንደኛ ነህ ለካ (፪x)

ምነው ሌላ ቋንቋ
ሌላ ሌላ ቋንቋ
ቢኖረኝ /ቢፈጠር/ ልብን የሚያረካ (፪x)

አልወጣልህ አለኝ ከልቤ
እስቲ ላመስግንህ ጌታዬ ጌታዬ

አዝ
ያለኝ ይሄ ነው ያለኝ (፬x)

አጣሁልህ እየሱስ አንተን መሳይ
የከበረ በምድር በሰማይ
ፍቅርህ ልቤን ጥብቅ አድርጐ ይዞታል
እስቲ ዘምር አመስግን ያሰኘኛል

ሥምህ የከበረ የገነነ ነዉ ነዉ
ዝናህ የከበረ የገነነ ነዉ ነዉ
ጌታ ነህ ጌታ ነህ ከሁሉ በላይ
እንዳንተ ያለ በምድር የለም በሰማይ (፪x)

ሰው ያለኝ ይሄ ነው እያለ ሲያወራ
የእኔ ግን ጌታ ነው የለውም እኩያ (፪x)

አዝ
ያለኝ ጌታ ነው ያለኝ (፪x)
ያለኝ እርሱ ነው ያለኝ (፪x)

አምልኬ አልጠግብ አልኩ ጌታዬ
አንግሼ አልጠግብህም አልኩ ወዳጄ
አጣሁ አጣሁኝ አንተን የሚተካ
በምድር በሰማይ አንደኛ ነህ ለካ (፪x)

ምነው ሌላ ቋንቋ
ሌላ ሌላ ቋንቋ
ቢኖረኝ /ቢፈጠር/ ልብን የሚያረካ (፪x)

አልወጣልህ አለኝ ከልቤ
ውለታህ በዛብኝ ጌታዬ ጌታዬ
አልወጣልህ አለኝ ከልቤ
እስቲ ላመስግንህ ጌታዬ ጌታዬ

አዝ
ያለኝ ይሄ ነው ያለኝ (፬x)