ባለፈው ፡ ዘመኔስ ፡ ብዙ ፡ አጥፍቻለው
ባለማስተዋሌም ፡ ተጎድቻለው
ፍቅርን ፡ የተሞላህ ፡ ባታግዘኝ ፡ ኖሮ
እንዴት ፡ ይዘለቃል ፡ የዚህ ፡ ምድር ፡ ኑሮ
አሁንም ፡ ጌታዬ ፡ መንገዴን ፡ አደራ
ታዳጊ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ በሚገጥመኝ ፡ መከራ (2)
አዝ፦
መንገዴን ፡ አደራ ፡ አደራ
በቀረው ፡ ዘመኔስ ፡ ስራህን ፡ ስራ (2)
ጉዞዬ ፡ ከብዶብኝ ፡ ስወድቅ ፡ ስነሳ
እዚህ ፡ ደርሻለው ፡ በብዙ ፡ አበሳ
የቀረው ፡ ዘመኔስ ፡ ብሩህ ፡ ይሁንልኝ
ኢየሱሴ ፡ በኃይልህ ፡ ስራዬን ፡ ስራልኝ
የኋላዬን ፡ ልርሳ ፡ ወዳንተ ፡ ልጠጋ
ከፊቴ ፡ ያለውን ፡ ለመያዝ ፡ ልዘርጋ
አዝ፦
መንገዴን ፡ አደራ ፡ አደራ
በቀረው ፡ ጉዞዬስ ፡ ስራህን ፡ ስራ(2)
በስጋዬ ፡ ምኞት ፡ በከንቱ ፡ ስገዛ
ስንት ፡ ጊዜ ፡ አቃጠልኩ ፡ እንዲሁ ፡ በዋዛ
ለቅዱሱ ፡ አደራህ ፡ ታማኝ ፡ አልነበርኩም
እንደልብህ ፡ ደስታም ፡ አላገለገልኩም
እንግዲህስ ፡ ጌታ ፡ ስራብኝ ፡ እንደሰው
(በጭንጋፉ) በትንሹ ፡ ባሪያ ፡ ከሁሉም ፡ በማንሰው