Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Weletaw


ዘማሪ ፡ አገኘሁ ፡ ይደግ ርዕስ ፡ ውለታው አልበም ፡ ኃይለኛ ፡ እንዳንተ ፡ የለም

አዝ
ውለታው (፫x) ውለታው ፡ በዛብኝ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው ፡ በዛብኝ
ናዝራዊው ፡ ወዳጄ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ

ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ በመስቀል ፡ ሞተልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
በእንጨት ፡ ተንጠልጥሎ ፡ እርግማን ፡ ሆነልኝ ፡ ውለታው ፡ በዛብኝ
በከበረ ፡ ደሙ ፡ በውድ ፡ ዋጋ ፡ ገዛኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ሲጠራኝ ፡ ብቻዬን ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ አበዛኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ

ከአዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ

አዝ
ውለታው (፫x) ውለታው ፡ በዛብኝ
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው ፡ በዛብኝ
ናዝራዊው ፡ ወዳጄ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ

ከበለስ ፡ ዛፍ ፡ በታች ፡ ተቀምጬ ፡ አይኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ተንኮል ፡ የሌለብህ ፡ የእስራኤል ፡ ልጅ ፡ አለኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ታማኝ ፡ አድርጐ ፡ ቆጥሮ ፡ ለአገልግሎት ፡ ሾመኝ ፡ ውለታው ፡ በዛብኝ
ኢየሱሴን ፡ መጠጋት ፡ ለእኔ ፡ እጅግ ፡ ጠቀመኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ

ከአዕምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ

አዝ
ውለታው (፫x) (ውለታው ፡ በዛብኝ)
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው ፡ በዛብኝ
ናዝራዊው ፡ ወዳጄ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ

በግ ፡ እረኛ ፡ ነብረኩ ፡ ገና ፡ ብላቴና
ውለታው ፡ በዛብኝ
እግዚአብሔር ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ አገኘሁኝና
ውለታው ፡ በዛብኝ
እኔን ፡ በናቁኝ ፡ ፊት ፡ ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ንጉሡ ፡ ሊያከብረኝ ፡ ወደ ፡ እልፊኙ ፡ አገባኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ

ሰው ፡ ላደረገልኝ ፡ እንደዚህ ፡ ዛሬ
ሥሙን ፡ ላወድሰው ፡ በዝማሬ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ
እንዴት ፡ ላመስግነው ፡ ይህንን ፡ ጌታ (7)

አዝ
ውለታው (፫x) (ውለታው ፡ በዛብኝ)
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ
ውለታው (፫x) ውለታው ፡ በዛብኝ
ናዝራዊው ፡ ወዳጄ ፡ ብዙ ፡ አደረገልኝ
ውለታው ፡ በዛብኝ።