Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Yeiemahus Mengedegnoch

ዘማሪ ፡ አገኘሁ ፡ ይደግ ርዕስ ፡ የኤማሁስ ፡ መንገደኞች አልበም ፡ ኃይለኛ ፡ እንዳንተ ፡ የለም

የተስፋን ፡ ቃል ፡ የሰጣችሁ ፡ የታመነ ፡ ነውና በስፍራችሁ ፡ ሆናችሁ ፡ ጠብቁት ፡ ታገሱና እግዚአብሔር ፡ አይጨክንም ፡ ያስብላችኋል እርሱ ፡ ሰብሯችኋልና ፡ እርሱ ፡ ይጠግናችኋል

አዝ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ

ጠውልጋችሁ ፡ ዝላችኋል ፡ የምትሉትን ፡ አታውቁም ስንፍናና ፡ ዝንጉነትን ፡ ለምን ፡ ከእናንተ ፡ አታርቁም እግዚአብሔር ፡ እረስቶናል ፡ እባካችሁን ፡ አትበሉ የሚበዣችሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ለቃሉ

አዝ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ

ይቤዠናል ፡ ብለን ፡ ነበረ ፡ ተስፋ ፡ ያደረግነው ለካስ ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ እንደዚህ ፡ ዓይነት ፡ አምላክ ፡ ነው ስለምን ፡ እንደዚህ ፡ ትናገራላችሁ ጌታችን ፡ ከሞት ፡ ተነስቶ ፡ አሁን ፡ እኮ ፡ አለ ፡ አብሯችሁ

አዝ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ

ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ ፡ ስፍራችሁን ፡ ለቃችኋል እግዚአብሔር ፡ ያላችሁን ፡ በሙሉ ፡ ዘንግታችኋል የገባላችሁን ፡ ተስፋ ፡ እናንተ ፡ እንኳን ፡ ብትረሱ እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ አይረሳም ፡ ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ

አዝ የኤማሆስ ፡ መንገደኞች የጌታ ፡ ደቀ ፡ መዝሙሮች ወደ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ተመለሱ ከሞት ፡ ተነስቷል ፡ ንጉሡ