Agegnehu Yideg/Haylegna Endante Yelem/Mesgana Keber


ዘማሪ ፡ አገኘሁ ፡ ይደግ ርዕስ ፡ ምሥጋና ፡ ክብር አልበም ፡ ኃይለኛ ፡ እንዳንተ ፡ የለም

ኃጥያተኞች ፡ ሳለን ፡ እግዚአብሔር ፡ አሰበን ከፋንዲያ ፡ ላይም ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አረገን በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ሥማችንን ፡ ጻፈው የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው በሕይወት ፡ መዝገብ ፡ ላይ ፡ ሥማችንን ፡ ጻፈው የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው

አዝ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x) ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)

አዕምሮን ፡ የሚያልፍ ፡ ሰላሙን ፡ ሰጥቶናል በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ሁሌ ፡ ደስ ፡ ይለናል ምድር ፡ ብትናውጥ ፡ አንዳች ፡ አንሆንም የመረጠን ፡ አምላክ/ኢየሱስ ፡ ፈጽሞ ፡ አይተወንም (፪x)

አዝ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x) ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)

ኢየሱስ ፡ እረኛችን ፡ ጠባቂያችን ፡ ሆኗል በሞት ፡ ጥላም ፡ ብንሄድ ፡ ምንድን ፡ ያስፈራናል በለመለምው ፡ መስክ ፡ በእረፍት ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ሁሌ ፡ ይመራናል ፡ ወደ ፡ እውነት ፡ መንገድ (፪x)

አዝ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x) ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ከላይ ፡ በድንቅ ፡ ጐብኝቶናል በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ በእሳት ፡ አጥምቆናል በመከራም ፡ ጊዜ ፡ እንደሰታለን እንደ ፡ ዘንባባ ፡ ዛፍ ፡ እንለመልማለን በመከራም ፡ ጊዜ ፡ እንደሰታለን በሽምግልናችን ፡ እንለመልማለን

አዝ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ክብር (፪x) ለአምላካችን ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)