እጠራዋለሁ ፡ ስምህን (Eterawalew Simihini) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

፩
(1)

ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Single Mezmurs)

ቁጥር (Track):

፪ (2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

እጠራዋለሁ ስምህን

እየሱስ ብዬ ብውል ባድር የማይሰለቸኝ
የዳንኩበት ስም ሰላም የሆነኝ (፪x)

መዳኒቴ ነው እፎይ ያልኩበት
እጠራዋለሁ ስምህን
ከክፉ ሁሉ ያመለጥኩብህ
እጠራዋለሁ ስምህን
አቅም ቢደክም ቢዝል ጉልበቴ
እጠራዋለሁ ስምህን
በሕይወት አቆምከኝ እንደ ትምክቴ
እጠራዋለሁ ስምህን

ስምህን ልወድስ ልቀድሰው
እየሱስ የሚለው ስም ክብር ሃይል አለው (፪x)

እየሱስ ብዬ ብውል ባድር የማይሰለቸኝ
የዳንኩበት ስም ሰላም የሆነኝ (፪x)

ፍቅሩ ማለዳ ሲቀሰቅሰኝ
እጠራዋለሁ ስምህን
በህልውናው ውስጤን ሲሞላው
እጠራዋለሁ ስምህን
የደስታዬ ምንጭ ጉልበቴ
እጠራዋለሁ ስምህን
የልቤ ሰላም የውስጥ እረፍቴ
እጠራዋለሁ ስምህን

ስምህን ልወድስ ልቀድሰው
እየሱስ የሚለው ስም ክብር ሃይል አለው (፬x)