እግዚአብሔር ፡ ትክክል (Egziabher Tikikil) - ዮሴፍ ፡ ካሳ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ዮሴፍ ፡ ካሳ
(Yosef Kassa)

፩
(1)

ነጠላ ፡ መዝሙሮች
(Single Mezmurs)

ቁጥር (Track):

፩ (1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዮሴፍ ፡ ካሳ ፡ አልበሞች
(Albums by Yosef Kassa)

ጻድቅ ነህ በሥራህ አትሳሳትም
እንዲህ አድርግ አትባልም

በዚህ ዓለም ገና ምንም ሳይኖር
ቅድሞም ያውቀኛል ሳልፈጠር
ህይወቴን ሁሉ ያውቀዋል ጌታ
ምን እንደሚሆን ምን እንዲመጣ
የማይሆነውም አይሆንምና
ሚሆንው ሊሆን ግድ ነውና
የስንፍና ቃል ከአፌ አይወጣ
ይህን ነው ምለው ጻድቅ ነው ጌታ

እግዚአብሔር ትክክል (፫X) ነህ አንተ
በሥራህ ጻድቅ ነህ

ማን እንዲህ እንዲያ አድርግ ይልሃል
ማንስ አስተያየት ይሰጥሃል
ሁሉም በፈቃድህ ታደርጋለህ
እግዚአብሔር አንተ ጻድቅ ነህ

ጻድቅ ነህ በሥራህ አትሳሳትም
እንዲህ አድርግ አትባልም

የለመንኩህን የጠየቅኩህን
አርግልኝ ቢዬ ሙጥኝ ያልኩህን
አይሆንም ብለ ስትከለክልኝ
ልቤም ሲከፋ አልገባ ሲልኝ
አባት ለልጁ እንደሚራራ
የሚረባኝ ታውቃለህና
ይህ ነው ትክክል አንተ ያልከው
ሃሳብህ ይሁን የፈቀድከው

እግዚአብሔር ትክክል (፫X) ነህ አንተ
በሥራህ ጻድቅ ነህ

ማን እንዲህ እንዲያ አድርግ ይልሃል
ማንስ አስተያየት ይሰጥሃል
ሁሉም በፈቃድህ ታደርጋለህ
እግዚአብሔር አንተ ጻድቅ ነህ

በቃሽ ነፍሴ ሆይ ስሚኝ
በእግዚአብሔር ታመኚ
ሁሌ ትክክል ነው እርሱ
ጻድቅ ነው ንጉሱ