ላደረክልኝ ፡ የምመልሰው (Ladereklign Yemimelisew) - ታምራት ፡ ሃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ታምራት ፡ ሃይሌ
(Tamirat Haile)

፬
(4)

እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
(Egziabher Terarayen Anagerew)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 5:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የታምራት ፡ ሃይሌ ፡ አልበሞች
(Albums by Tamirat Haile)

ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና (፪x)

አንደበት ፡ የለኝ ፡ ሥምህን ፡ ልጠራ
ምላስም ፡ የለኝ ፡ ሥራህን ፡ ላወራ
ልናገርም ፡ ብል ፡ ጊዜም ፡ አይበቃ
ተመስገን ፡ ብዬ ፡ በአጭሩ ፡ ላብቃ (፪x)

አዝ
ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና (፪x)

በፍቅር ፡ ቃልህ ፡ ልቤን ፡ ስትመታ
ነፍሴን ፡ ሥጋዬን ፡ ከእስር ፡ ስትፈታ
ምን ፡ አለኝና ፡ ምኔን ፡ ልክፈልህ
ከተቀበልኸኝ ፡ ክበር ፡ ልበልህ (፪x)

አዝ
ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና(፪x)

ከትቢያ ፡ አንስተህ ፡ ሰው ፡ ስታደርገኝ
በነፍስ ፡ በሥጋ ፡ ስትባርከኝ
ሰማያዊ ፡ ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ሲሞላ
ተመስገን ፡ እንጂ ፡ የለኝም ፡ ሌላ(፪x)

አዝ
ላደረግህልኝ ፡ የምመልሰው
አንዳች ፡ የለኝም ፡ እጄም ፡ ባዶ ፡ ነው
እንካ ፡ ተቀበል ፡ የአፌን ፡ ምሥጋና
በእጄ ፡ ያለው ፡ ይኸው ፡ ነውና (፪x)