Tamrat Haile/Egziabhier Terarayien Anagerew/Andun Seneshegnew
ዘማሪ ፡ ታምራት ፡ ሃይሌ ርዕስ ፡ አንዱን ፡ ስንሸኘው አልበም ፡ እግዚአብሔር ፡ ተራራዬን ፡ አናገረው
አዝ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ ፡ ምድረበዳ የማይደፈን ፡ ቀዳዳ ቋጡ ፡ ጠብ ፡ አላለም ፡ ጉድጓዱም ፡ አልሞላ አንዱን ፡ ስንሸኘው ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ ሌላው እንቆቅልሹ ፡ ሺህ ፡ ችግሩም ፡ እልፍ ፡ ነው ጌታን ፡ አምነን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታን ፡ ይዘን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታ ፡ ካለ ፡ እርፍ ፡ ነው
ልንደላደል ፡ ልንመቻች ቀን ፡ ሙሉ ፡ ስንሮጥ ፡ እላይ ፡ እታች መቼ ፡ ሞላልን ፡ እንዲህ ፡ እየጣርን ነፍሳችን ፡ እረፍት ፡ አጥታ ፀሐይ ፡ ማዘቅዘቋን ፡ መምሸቱን ፡ አውቀን ወደ ፡ እግዚአብሄር ፡ ጉያ ፡ እንግባ ፡ ፈጥነን
አዝ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ ፡ ምድረበዳ የማይደፈን ፡ ቀዳዳ ቋጡ ፡ ጠብ ፡ አላለም ፡ ጉድጓዱም ፡ አልሞላ አንዱን ፡ ስንሸኘው ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ ሌላው እንቆቅልሹ ፡ ሺህ ፡ ችግሩም ፡ እልፍ ፡ ነው ጌታን ፡ አምነን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታን ፡ ይዘን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታ ፡ ካለ ፡ እርፍ ፡ ነው
በመሸማቀቅ ፡ በሰቀቀን በሃሩር ፡ ፀሐይ ፡ በእኩለ ፡ ቀን ውኃ ፡ ፍለጋ ፡ ከአድማስ ፡ ወዲያ የተጓዘችው ፡ በሰማሪያ አምስቱም ፡ ባሎቿ ፡ ያልሰጧትን ፡ ደስታ ኢየሱስን ፡ ስታገኝ ፡ ቋጠሮዋ ፡ ተፈታ
አዝ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ ፡ ምድረበዳ የማይደፈን ፡ ቀዳዳ ቋጡ ፡ ጠብ ፡ አላለም ፡ ጉድጓዱም ፡ አልሞላ አንዱን ፡ ስንሸኘው ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ ሌላው እንቆቅልሹ ፡ ሺህ ፡ ችግሩም ፡ እልፍ ፡ ነው ጌታን ፡ አምነን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታን ፡ ይዘን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታ ፡ ካለ ፡ እርፍ ፡ ነው
እንድንጮህ ፡ አባት ፡ አባት ፡ ብለን እግዚአብሔር ፡ ሰጠን ፡ መንፈሱን በሰማይም ፡ ቤት ፡ ሰርቶልናል በቅርቡም ፡ መጥቶ ፡ ይወስደናል ወላጅ ፡ አልባ ፡ ልጆች ፡ አይደለንም ፡ እኛ ጌታችን ፡ በክብር ፡ ይመጣል ፡ ዳግመኛ
አዝ የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ ፡ ምድረበዳ የማይደፈን ፡ ቀዳዳ ቋጡ ፡ ጠብ ፡ አላለም ፡ ጉድጓዱም ፡ አልሞላ አንዱን ፡ ስንሸኘው ፡ ከተፍ ፡ ይላል ፡ ሌላው እንቆቅልሹ ፡ ሺህ ፡ ችግሩም ፡ እልፍ ፡ ነው ጌታን ፡ አምነን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታን ፡ ይዘን ፡ እርፍ ፡ ነው ጌታ ፡ ካለ ፡ እርፍ ፡ ነው
የቤተልሔም ፡ ረሃብ ፡ ያልፋል ወደ ፡ ሞአብስ ፡ ምን ፡ ያለፋል ያለመጠበቅ ፡ ያለማረፍ ለመዘረፍ ፡ ነው ፡ ለመገፈፍ እግዚአብሔር ፡ ሕዝቡን ፡ በርግጥ ፡ ይጐበኛል ሁሉም ፡ ሰው ፡ በጊዜው ፡ ዳኝነት ፡ ያገኛል