ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ (Joro Yalew Yesma) - ታምራት ፡ ኃይሌ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

በጐ ፡ ነው ፡ (፬X)
የእግዚአብሔር ፡ ዓላማ
ጆሮ ፡ ያለው ፡ ይስማ



የጌታን መከራ ሞቱን እንዳትረሱ

ለምን ጣፋጭ ብቻ መራራም ቅመሱ

በደስታ ጊዜ እንደምትዘምሩ

በመከራም መሃል ኢየሱስን አክብሩ


በጐ ፡ ነው


የምታመልከው አምላክ መዋጋትን ያውቃል

በእሳት ውስጥ አልፎ ከእሳት ያወጣል

አንተም በህይወትህ አምላክህን ምሰል

በረከት ብቻ አይደል መከራም ተቀበል


በጐ ፡ ነው


የመከራ እንጀራ የመከራ ውኅ

ቢያንከራትትህ በአለም በረሃ

ክረምት ይመጣና ያለመልምሃል

በጠላቶችህ ፊት በዘይት ይቀባሃል