የምሥራች (Yemeserach) - መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

አዝማች
(የምስራች ፡ የምስራች ፡ ይኸው
የምስራቹ ፡ ጽዮን ፡ ደርሰናል ፡ አትሰልቹ
ያቻት ፡ ባሻገር ፡ የጻድቃኖች ፡ አገር) (፪x)

ዘመናት ፡ ቆጥረን ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል
እንግዲህ : ልናርፍ ፡ ሰዓቱ ፡ ደርሷል
ከተራራው ፡ ጐን ፡ የምትታየው
ጽዮን ፡ ያች ፡ ናት ፡ ድንቋ ፡ ቤታችን

አዝ
የምስራች

ቅጥሯን ፡ ልንረግጥ ፡ ምንም ፡ አልቀረን
እፎይ ፡ ለማለት ፡ ጽዮን ፡ ቤታችን
ከማዶ ፡ ያለው ፡ የአትክልት ፡ ቦታ
የጽዮን ፡ ቤት ፡ ነው፡ የሰጠን ፡ ጌታ

አዝ
የምስራች

ተራራ ፡ ጋርዶን ፡ ሳናያት ፡ ነበር
አሁን ፡ ምን ፡ ቀረን ፡ ከጽዮን ፡ ቤት
አቤት ፡ ማማሩ ፡ አበባው ፡ መስኩ
ግምቴ ፡ ይሄ ፡ ነው፡ የውበት ፡ ልኩ

አዝ
የምስራች