Meserete Kristos Choir/Mesgana Melkam New/Endiet Talaq Neh
ዘማሪ ፡ መሠረተ ፡ ክርስቶስ ፡ መዘምራን ርዕስ ፡ እንዴት ፡ ታላቅ ፡ ነህ አልበም ፡ ምሥጋና ፡ መልካም ፡ ነው
አዝ አቤት ፡ እንዴት ፡ ትላቅ ፡ ነህ እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለውጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ (፪x)
በቃ ፡ አልፈልግም ፡ ልቤን ፡ ውሰደው አእምሮዬን ፡ ግዛው ፡ ለአንተ ፡ አድርገው ዝም ፡ ልበልና ፡ ኃይልህን ፡ ልመልከት ሌላው ፡ ሀሳቤ ፡ ይብቃ ፡ ይከተት አዝ አቤት ፡ እንዴት ፡ ትላቅ ፡ ነህ እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለውጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ
ሌት ፡ በመኝታ ፡ እንዳስብ ፡ አንተን ቀን ፡ በሥራዬ ፡ እንዳጠነጥን መና ፡ ለነፍሴ ፡ እርካታና ፡ ደስታ ክብርህን ፡ ላስበው ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
አዝ አቤት ፡ እንዴት ፡ ትላቅ ፡ ነህ እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለውጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ
እጄን ፡ በአፌ ፡ ላይ ፡ አድርጌ ፡ ተደነኩ ሥራህንም ፡ ሳየው ፡ በደስታ ተሞላሁ በእውነት ፡ ተረዳሁ ፡ የአንተን ፡ ታላቅነት እንዲሁም ፡ አስተዋልኩ ፡ የእኔን ፡ ታናሽነት
አዝ አቤት ፡ እንዴት ፡ ትላቅ ፡ ነህ እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለውጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ
ለአንተ ፡ የሚገባህ ፡ ክብርህን ፡ ለመስጠት በመንፈስ ፡ ሳስብህ ፡ ያኔ ፡ ተረዳሁት አሁን ፡ ቃልኪዳኔ ፡ የመጨረሻው ተዋርጄ ፡ እንድኖር ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ የምሻው
አዝ አቤት ፡ እንዴት ፡ ትላቅ ፡ ነህ እንዴት ፡ ታማኝ ፡ ነህ እንዴት ፡ ፍፁም ፡ ነህ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የማትለውጥ የፍቅር ፡ አባት ፡ ጸንተህ ፡ ትኖራለህ (፪x)