ቅዱስ ፡ ቅዱስ (Qedus Qedus) - ምህረት ፡ ኢተፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ምህረት ፡ ኢተፋ
(Meheret Etefa)

፫
(3)

ባለግርማ
(Balegirma)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

፮ (6)

ርዝመት (Len.): 5:12
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የምህረት ፡ ኢተፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Meheret Etefa)

ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው
ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው
ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው
ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው

ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ እያሉህ
ኪሩቤል ሱራፌል እንደሚያመልኩህ
መላዕክት በአንድነት እንደሚሰግዱልህ
እኔም አመልክሀለው ይኸው በፊትህ(፪*)

ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው
ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው
ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው
ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው

የምድርን ውሆች በእፍኝህ ሰፍረሀል
የአለምን ተራሮች በሀይልህ አፅንተሀል
ሽማግሌዎች ወድቀው ፊትህ ይሰግዱልሀል
አቤቱ አምላክ ሆይ ማንስ ይመስልሀል(፪*)

ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው
ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው
ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው
ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው

ቅዱስ ቅዱስ ብለው ሲዘምሩልህ
ጳውሎስ እና ሲላስ ከልብ ሲያመልኩህ
የወህኒውን መሰረተ አናወጠ ሀይልህ
በአምልኮ ውስጥ መጣ ታላቁ ክብርህ(፪*)

ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው
ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው
ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው
ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው

አእዋፍ ለእኛ የማይገባን ድምፃቸው
ከትንሽ ጀምሮ ሁሉም በየቋንቋው
ክበር ይሉሀል ያመሰግኑሀል
እውነት ነው ጌታ ሆይ ክብር ይገባሀል(፪*)

ቅዱስ ቅዱስ በክብር ያለኸው
ዙፋንህ ከጥንት እስከ ዘላለም ነው
ክብር ሞገስ ሁልጊዜም አብሮህ ነው
ሀሌ ሀሌሉያ እኔ አመልክሀለው