Kalkidan Tilahun/LeEgziabhier Qelal New/Weha Weha Endayel

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
አልበም ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ቀላል ፡ ነው
ርዕስ ፡ ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል

ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል ፡ ሕይወቴን ፡ አጣፍጠህ
ይሄ ፡ ነው ፡ የማይባል ፡ ልዩ ፡ ጣዕም ፡ ሰጥተህ (2)
መኖር ፡ አስመኘኸኝ ፡ መኖር ፡ መኖር ፡ አለኝ
መኖር ፡ የሚያስወድድ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለኝ

ውኃ ፡ ውኃ ፡ እንዳይል ፡ ሕይወቴን ፡ አጣፍጠህ
ይሄ ፡ ነው ፡ የማይባል ፡ ልዩ ፡ ጣዕም ሰጥተህ (፪x)
መኖር ፡ አስመኘኸኝ ፡ መኖር ፡ መኖር ፡ አለኝ
መኖር ፡ የሚያስወድድ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለኝ (፪x)

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ (፫X)
እንደገና ፡ አከብርሃለሁ (፫X)

ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ እስካሁን ፡ የባረከኝ
አንተ ፡ አልበቃህም ፡ ዎይ
ባርከኸኝ ፡ ባርከኸኝ (፪x)
ይበቃኝ ፡ ነበረ ፡ ራስህን ፡ የሰጠኸኝ
አንተ ፡ አልበቃህም ፡ ዎይ ፡ ሰጠኸኝ ፡ ሰጠኸኝ (፪x)

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ
እንደገና ፡ እሰጥሃለሁ ፡ እንደገና አሃአሃ

ገነት ፡ ገብቻለሁ ፡ እዚሁ ፡ ምድር ፡ ላይ
አልጠብቅም ፡ ገና ፡ እስክሄድ ፡ ሠማይ ፡ ላይ (፪x)
ገነቴ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ እዚሁ ፡ ምድር ፡ ላይ
እኔ ፡ አልጠብቅም ፡ ገና ፡ እስክሄድ ፡ ሠማይ ፡ ላይ (፪x)

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ
እንደገና ፡ አከብርሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ

አልጠገብኩምና ፡ አልረካሁምና
እኔ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ዛሬም ፡ እንደገና
አልጠገብኩምና ፡ አልረካሁምና
አመሰግናለሁ ፡ ዛሬም ፡ እንደገና

እንደገና ፡ አመልክሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ
እንደገና ፡ አሃአሃ
እንደገና ፡ አከብርሃለሁ ፡ እንደገና ፡ አሃአሃ
እንደገና ፡ አሃአሃ (፪x)