Kalkidan Tilahun/Beyet Hager New Egziabhier/Ejeg Yemimer
ዘማሪ ፡ ቃልኪዳን ፡ ጥላሁን
ሌላ ፡ ሥም ፡ ሊሊ
ርዕስ ፡ እጅግ ፡ የሚምር
አልበም ፡ በየት ፡ ሃገር ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ጻድቅ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ስራህ ፡ ትክክል
የማታደላ ፡ የማትበድል
ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለው
አቤት ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ስራህ ፡ ድንቅ ፡ ነው
ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x)
ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x)
ደግሜ ፡ ደጋግሜ ፡ እባርክሃለሁ
ምሥጋና ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው
ማለዳ ፡ በምሥጋና ፡ አፌን ፡ እከፍታለሁ
ከአንደበቴ ፡ ፍሬ ፡ ለአንተው ፡ እነግራለሁ
ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x)
ምላሴ ፡ ጽድቅህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ምሥጋናህን ፡ ይናገራል (፫x)
አዝ
እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ
አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፪x)
እንኳንስ ፡ ምረሄኝ ፡ ቀርቶልኝ ፡ አበሳ (፪x)
እኔስ ፡ ምሥጋናዬን ፡ ሁልጊዜው ፡ አልረሳ (፪x)
ምህረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ጠንክራለችና (፪x)
ኃይሌ ፡ ታድሶልኝ ፡ ቆምኩኝ ፡ እንደገና (፪x)
አዝ
እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ
አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፬x)
ማዳኑን ፡ አስታውቆ ፡ ጽድቁንም ፡ ገለጠ (፪x)
ከእኛ ፡ መተላለፍ ፡ ምህረቱ ፡ በለጠ (፪x)
በሞገሱ ፡ ጋሻ ፡ እየከለለን (፪x)
ከአዳነን ፡ በኋላ ፡ ምህረቱ ፡ ያዘን (፪x)
አንድ ፡ ላይ ፡ ተስማሙ ፡ እውነትና ፡ ምህረት (፪x)
መግባትም ፡ ተቻለን ፡ እግዚአብሔር ፡ ካለበት (፪x)
ጻድቅ ፡ ፈራጅ ፡ ሲሆን ፡ እንከን ፡ የሌለበት (፪x)
አልፈረደብኝም ፡ ምህረቱ ፡ አይሎበት (፪x)
አዝ
እጅግ ፡ የሚምር ፡ የሚራራ
አምላክ ፡ ነውና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና ፡ የእኔ ፡ ጌታ
ይድረሰው ፡ ምሥጋና
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይድረሰው ፡ ምሥጋና (፬x)
ጌታ ፡ እልሃለሁ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪x)
አምላክ ፡ እልሃለሁኝ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪x)
አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፪x)
ይገባሃል ፡ የአንደበቴ ፡ ቃል
ይገባሃል ፡ የአፌ ፡ ምሥጋና
ይገባሃል ፡ ልዘምርልህ
ይገባሃል ፡ ላገለግልህ
እኔ ፡ አምላክ ፡ እልሃለሁኝ ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ (፭x)
እስከዛሬ ፡ ተመስገን ፡ ብያለሁ ፡ ተባረክ ፡ ብያለሁ ፡ አሃ
ከፍ ፡ በል ፡ ብያለሁ ፡ እስከዛሬ ፡ ተመስገን ፡ ብያለሁ
ተባረክ ፡ ብያለሁ ፡ አሃ ፡ ከፍ ፡ በል ፡ ብያለሁ
ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል
ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል
ደግሞ ፡ አሁን ፡ አሁን ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ጌታ
አሁን ፡ ምን ፡ ልበል
ደግሞ ፡ ዛሬ ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል
ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል ፡ ዛሬ ፡ ምን ፡ ልበል
ይገባሃል ፡ የአንደበቴ ፡ ቃል
ይገባሃል ፡ የአፌ ፡ ምሥጋና
ይገባሃል ፡ ላገለግልህ
ይገባሃል ፡ ልዘምርልህ
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ (፬x)