ነፍሴን ፡ የሚያረካት (Nefsen Yemiyarekat) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

፮
(6)

4
(4)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2022)
ቁጥር (Track):

፰ (8)

ርዝመት (Len.): 11:17
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ማን ፡ ተወኝ ፡ ማን ፡ ተቀየረ ፡ እያልኩኝ ፡ ሳዝን ፡ መኖሬ
አብቅቷል ፡ ልቤ ፡ በርትቷል ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለ ፡ ጐኔ
የማንም ፡ ፊት ፡ እንደቀድሞ ፡ ባይሆን ፡ ከእኔ ፡ ጋር
ሃሴት ፡ ከ'ኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡መሽቶ ፡ ሲነጋ ፡ ፪*
 
ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ ምሥጋና ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው
ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ አምልኮ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው
የአንተ ፡ ፊት ፡ ተቀብሎኛል ፡ እጅህ ፡ አቅፎኛል
 <ጌታ ፡ ሆይ ፡በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል > ፡ ፰*


ላይሰለጥንብኝ ፡ ልቤ ፡ ላይ ፡ ጨለማ
ፈገግ ፡ ካለልኝ ፡ የአንተ ፡ ፊት ፡ ከበራ
እረክታለች ፡ ነፍሴ ፡ በማትለወጠው
ሁልጊዜ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ነው ፡ ማየው
የበራልኝ ፡ ፊትህ
ፈገግ ፡ ያለው ፡ ፊትህ
ጨለማዬን ፡ አሸንፏል
ጌታ ፡ በአንተ ፡ ደስተኛ ፡ ነኝ

ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ ምሥጋና ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው
ነፍሴን ፡ የሚያረካት ፡ አምልኮ፡ 'ሚሞላት ፡ ይሄ ፡ ነው
የአንተ ፡ ፊት ፡ ተቀብሎኛል ፡ እጅህ ፡ አቅፎኛል
 <ጌታ ፡ ሆይ ፡በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል > ፡ ፰*

ማን ፡ ተወኝ ፡ ማን ፡ ተቀየረ ፡ እያልኩኝ ፡ ሳዝን ፡ መኖሬ
አብቅቷል ፡ ልቤ ፡ በርትቷል ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላለ ፡ ጐኔ
የማንም ፡ ፊት ፡ እንደቀድሞ ፡ ባይሆን ፡ ከእኔ ፡ ጋር
ሃሴት ፡ ከ'ኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፡መሽቶ ፡ ሲነጋ ፪*