እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ብርሃኔ (Egziabeher New Brhane) - እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
እንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ
(Endale Woldegiorgis)

፮
(6)

1
(1)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ ፫ (2022)
ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 8:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የእንዳለ ፡ ወልደጊዮርጊስ ፡ አልበሞች
(Albums by Endale Woldegiorgis)

ጨለማዉ ከብርሃኔ በላይ አይደለም
ህመሜ ከመድኃኒቴ በላይ አይደለም
እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ
እግዚአብሔር ነው መድኃኒቴ

እንዳልደናገር እንዳይገባይ ግራ
አለ ብርሃኔ ፊቴን የሚመራ
እህ ስል ሳቃስት ፈዉስን ፈልጌ
ጤና የሚያደርገኝ የሚሆን መድኃኒቴ
እግዚአብሔር ነዋ ብርሃኔ
እግዚአብሔር ነዋ መድኃኒቴ

ጨለማዉ ከብርሃኔ በላይ አይደለም
ህመሜ ከመድኃኒቴ በላይ አይደለም
እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ
እግዚአብሔር ነው መድኃኒቴ

የሚያስፈራራኝ ክምሩ ጨለማ
ሊያስብለኝ የሚሻ የዉድቀትን ዜማ
ከፊቴ ተገፎ አምልጣለች ነፍሴ
ዛሬም አምላኬ ነው ብርሃን ፈዉሴ
እግዚአብሔር ነዋ ብርሃኔ
እግዚአብሔር ነዋ መድሃኒቴ

የምፈራው የማከብረው
ብርሃኔን እንጂ ጨለማን አይደለም
የምፈራው የማከብረው
መድኃኒቴን እንጂ ህመሜን አይደለም
የሚያስፈራ እግዚአብሔር ብቻ
ሚያስደነግጥ እግዚአብሔር ብቻ

ጨለማዉ ከብርሃኔ በላይ አይደለም
ህመሜ ከመድኃኒቴ በላይ አይደለም
እግዚአብሔር ነው ብርሃኔ
እግዚአብሔር ነው መድኃኒቴ