እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ ቢሆን (Egziabhier Sewen Bihon) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ ቢሆን
ከቶ ፡ ምን ፡ በዋጠን
ምስኪን ፡ የሚያጽናና ፡ አምላክ ፡ ነውና (፪x)

ወዳጄ ፡ መስሎ ፡ ጠላት
ገብቶ ፡ በደከምኩበት
አቆሰለኝ ፡ አድብቶ
ጥርሱን ፡ አሳይቶ (፪x)

ፊት ፡ አይቶ ፡ አያደላ
አምላክ ፡ የደሃ ፡ ጥላ
ሁሉም ፡ እኩል ፡ ነው ፡ ለእርሱ
ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ (፪x)

ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተመስገን
የወደቅን ፡ እኛን ፡ ሰው ፡ አደረከን
የወደቅን ፡ እኛን ፡ ክብር ፡ አለበስከን (፪x)