ብልህ ፡ ሰው ፡ ነፍሱን ፡ ያድናል (Beleh Sew Nefsun Yadenal) - ደረጀ ፡ ከበደ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

አዝ፦ ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል
ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል
በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል

በልቡ ፡ አንተን ፡ ፈላጊ
ስምህን ፡ ጠሪ ፡ ይባረካል
በኑሮ ፡ የሚያስቀድምህ
የደስታን ፡ ካባን ፡ ይደርባል
ከእርኩሰት ፡ ታርቀዋለህ
በልቡ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ነግሰህ
ሰላምን ፡ በውስጡ ፡ አኑሮ
ይጓዛል ፡ ደስታን ፡ ጨምሮ

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል
ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል
በስምህ ፡ ትዕዛዝ ፡ ስር ፡ ያድራል


ከኋለኛው ፡ ሃዘን ፡ ይልቅ
የአሁኑን ፡ ጉስቁልና ፡ መርጦ
ጊዜያዊውን ፡ ተድላ ፡ ንቆ
ነፍሱን ፡ ከሥጋው ፡ ያየ ፡ አብልጦ
ብልህ ፡ ነው ፡ ጠቢብ ፡ አዋቂ
የሰማይ ፡ ሃገር ፡ ዘላቂ
ዘለዓለም ፡ እረፍትን ፡ አይቷል
ለተስፋው ፡ ምድር ፡ ተመርጧል

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ሕይወት ይመረጣል
ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል
በስምህ ታዛ ስር ያድራል

በለመለመ ፡ መስክ ፡ አድሮ
የጠራ ፡ ምንጭ ፡ ውኃ ፡ ጠጥቶ
በአምላኩ ፡ እንክብካቤ ፡ አድርጐ
መጓዙን ፡ የሰው ፡ ልጅ ፡ አጥላልቶ
ከስታለች ፡ ተርባ ፡ ነፍሱ
ታውኳል ፡ ሥጋ ፡ መንፈሱ
ይመለስ ፡ ሚወድ ፡ ይመለስ
ሳይወድቅ ፡ ጉልበቱ ፡ ሳይፈር

አዝ፦ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይመረጣል
ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል
በስምህ ታዛ ስር ያድራል (፬x)