From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation
Jump to search
|
|
|
|
|
|
|
(Volume)
|
አልበም (Album)
|
| ቁጥር (Track):
|
(Track)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
|
የደረጀ ፡ ከበደ ፡ አልበሞች (Albums by {{{Artist}}})
|
|
|
አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ልቀኝለት
በእግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
ነፍሴን ፡ አስጨንቋት ፡ የጠላቴ ፡ ጩኸት
አይኖቼን ፡ ባቀና ፡ ከላይ ፡ ስመለከት
ከመቅደሱ ፡ ሆኖ ፡ እምባዬን ፡ አበሰ
ያሰረኝን ፡ ገመድ ፡ ጌታ ፡ በጣጠሰ
አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ልቀኝለት
በእግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
የሞት ፡ ቀንበር ፡ ከቦኝ ፡ ያመፅ ፡ ፈሳሽ ፡ ውጦኝ
ሲኦል ፡ አፉን ፡ ከፍቶ ፡ ባጥንቴ ፡ አስቀርቶኝ
ስሞታ ፡ ነገርኩኝ ፡ ላምላኬ ፡ ሳልሰለች
እግዚአብሔር ፡ ተቆጣ ፡ ምድር ፡ ተናወጠች
አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ልቀኝለት
በእግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
ጠላቴን ፡ ሰበረ ፡ እንዳያንሰራራ
ከቁጣው ፡ ጢስ ፡ ወጣ ፡ ፍምም ፡ ከሱ ፡ በራ
ባእድ ፡ የረገጠኝ ፡ እንደመንገድ ፡ ጭቃ
ነፃነቴን ፡ ሰጠኝ ፡ መቆዘሜ ፡ አበቃ
አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ልቀኝለት
በእግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
ዛሬማ ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ ቀስት ፡ እገትራለሁ
በኮረብታ ፡ ቆሜ ፡ ምሥጋና ፡ እሰዋለሁ
ፅኑ ፡ እግር ፡ ለሰጠኝ ፡ የማይንሸራተት
ለናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ እጥፍ ፡ ልስገድለት
አዳኜ ፡ ኢየሱስ ፡ ገናናው
የእጄን ፡ ሰንሰለት ፡ በጠሰው
ተመስገን ፡ ልበል ፡ ልቀኝለት
በእግሩ ፡ ሥር ፡ ልውደቅ
ልስገድለት ፡ ይህም ፡ አነሰበት
|