Dereje Kebede/Adagnie Yesus/Ahadu Elalehugn

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

አሃዱ ፡ እላለሁ ፡ በምስጋና
አፌን ፡ እክፍታለሁ ፡ በምስጋና
እርሱ ፡ ያሰበልኝ ፡ በለጠና
የእኔ ፡ ከንቱ ፡ ሆኖ ፡ ቀርቷልና

ወጥቼ ፡ ወርጄ ፡ ብዙ ፡ አስቤአለሁ ፡ አውጠንጥኛለሁ
ልቤ ፡ እሰክሚጨነቅ ፡ በስጋ ፡ ጉዞ ፡ ተክለፍልፌአለሁ
ኋላ ፡ ግን ፡ በየሱስ ፡ ተሰብስቤያለሁ /፪

ፈቃዱን ፡ አውቄ ፡ በምስጋና ፡ ቃል ፡ ስሙን ፡ ጠርቼ
እውነተኛ ፡ ድምፁን ፡ ከአንደበቱ ፡ ጠርቶኝ ፡ ስምቼ
እርሱን ፡ እጠብቃለሁ ፡ ሌላውን ፡ ትቼ /፪

በከንቱ ፡ ነበረ ፡ መደካከሜ ፡ ላይ ፡ ታች ፡ ማለቴ
ነገ ፡ ዛሬ ፡ እንዲሆን ፡ በምኞት ፡ ሩጫ ፡ እጅግ ፡ መትጋቴ
አሁን ፡ ግን ፡ ልቀበል ፡ ከላይ ፡ ካባቴ /፪

እንግዲህ ፡ ካገኘሁ ፡ አጋዥ ፡ ከአርያም ፡ ሐሳቤን ፡ ጠቅላይ
ደቂቃም ፡ አታልፍም ፡ አይኔን ፡ አንስቼ ፡ ወደላይ ፡ ሳላይ
ድል ፡ ይላክልኛል ፡ ከሩቅ ፡ ከሰማይ /፪