በደስታ (Bedesta) - ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ዳንኤል ፡ አምደሚካኤል
(Daniel Amdemichael)

፯
(7)

ልዘምር
(Lezemer)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፲ (2019)
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 5:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የዳንኤል ፡ አምደሚካኤል ፡ አልበሞች
(Albums by Daniel Amdemichael)

በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው
የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው
ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ
የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ

ቅዱስ ነው ማስተዋሉ የማይመረመር
ቅዱስ ነው በሰማያት በክብር የሚኖር
ቅዱስ ነው ለዘመኑ ፍፃሜ የሌለው
ቅዱስ ነው ብርሃንን የተጎናፀፈው

በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው
የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው
ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ
የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ

ፃድቅ ነው የእውነት ዳኛ በፍርዱ ትክክል
ፃድቅ ነው ፍፁም ገዢ ፍትህ ማያጓድል
ፃድቅ ነው ትቢተኛውን እርሱ ያዋርዳል
ፃድቅ ነው ለትሁታን ፀጋን ይጨምራል

በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው
የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው
ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ
የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ

ህያው ነው ለዘላለም የማይለውጠው
ህያው ነው ትላንት ዛሬም ሁሌም ያው የሆነው
ህያው ነው መጀመሪያም መጨረሻም የለው
ህያው ነው ልዑል አምላክ ፍጥረት የሚያመልከው

በደስታ ላመልከው እጄን አነሳለው
የከበረ ስሙን አመሰግናለው አመሰግናለው
ቅዱስ ነው እግዚአብሔር ሁሉን የሚገዛ
የነገስታት ንጉስ የጌቶቹ ጌታ የጌቶቹ ጌታ