ያልደረስሁበት ፡ አክሊል ፡ አለኝ ኦ ፡ አምላኬ ፡ አሳስበኝ በምድርም ፡ እንዳይጠፋብኝ ስታክት ፡ ና ፡ አስጠንቅቀኝ ያልደረስሁበት ፡ ርስትም ፡ አለኝ እንዳላባክነው ፡ እርዳኝ በወጽመዱም ፡ እንዳያጸምደኝ ከሰይጣን ፡ ተንኮል ፡ ጠብቀኝ ኦ ፡ ጌታዬ ፡ ኦ ፡ የሞትህልኝ በቅዱስ ፡ እጅህ ፡ ደግፈኝ ወደ ፡ ሰማይም ፡ ስታደርሰኝ ያን ፡ ቅዱስ ፡ አክሊሌን ፡ ስጠኝ