ዓይኖቼ ፡ ወዳንተ ፡ ሲቀኑ (አይኖቼ ፡ ወዳንተ ፡ ሲቀኑ)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

። ዓይኖቼ ፡ ወዳንተ ፡ ሲቀኑ፥ ወዳንተ ፡ ሲቀኑ፥ ወዳንተ ፡ ሲቀኑ፣
። ኢየሱስ ፡ ቀናልኝ ፡ መንገዴ ፡ ብሩ ፡ ሆነ ፡ ቀኑ፤ ብሩህ ፡ ሆነ ፡ ቀኑ።

አንድ ፡ ችግር ፡ በመንገዴ ፡ እኔን ፡ ሲገጥመኝ፣
እዚያና ፡ እዚያ ፡ ስቅበዘበዝ ፡ መፍትሔ ፡ ላገኝ፣
ትዝ ፡ ትለኝና ፡ አንተን ፡ አስባለሁ፣
አይኖቼን ፡ ወዳንተ ፡ አቀናለሁ፤
ከችግሬም ፡ ቶሎ ፡ እፈታለሁ።
። ዓይኖቼ ፡ ወዳንተ ...

እመካብሀለሁ ፡ ጌታ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነህ፣
የሚያስፈራራኝን ፡ ሁሉ ፡ ትሽራለህ፤
የጠላት ፡ ቀስቱንም ፡ ሰብረህ ፡ አይቻለሁ፣
ኤልሻዳይ ፡ አምላኬ ፡ እታመንሃለሁ፤
ዘላለም ፡ በቤትህ ፡ መኖር ፡ መርጫለሁ።