ለትልቅ ፡ ሥራህ ፡ ሰነፍ ፡ ነኝ ኃይልን ፡ ፀጋን ፡ ላክልኝ ድካሜ ፡ ኃይልህን ፡ ይግለጥ ሥራዬ ፡ የአንተን ፡ ክብረት ፍጠር ፡ በልቤ ፡ ቅን ፡ እምነት ትህትናን ፡ አስርፅበት ላከኝ ፡ መስቀልህን ፡ ልከተል ከጭንቅ ፡ ከሞት ፡ መካከል እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ ለአንተ ፡ ነኝ የለም ፡ የሚታጣብኝ ከአሁን ፡ ምራኝ ፡ በአንተ ፡ ስምረት ቁምልኝ ፡ ዕለት ፡ ዕለት