ኢየሱስ ፡ በአንተ ፡ ድኜ ገንዘብህም ፡ ሁኜ በአንተ ፡ ጻድቅ ፡ ነኝ ግን ፡ በዓለም ፡ ነገር ልቤ ፡ እንዳይታሰር አንተ ፡ ጠብቀኝ ክፉው ፡ ጠላቴ ወጥመድ ፡ ለጥፋቴ ዘርግቶብኛል በእኔ ፡ ሲቀናብኝ ሃብቴን ፡ ሊነጥቅብኝ ሠርክ ፡ ይሸምቃል ስለዚህ ፡ ወደኛ አንተ ፡ ቸር ፡ እረኛ ናና ፡ ጠብቀን ታናሽ ፡ መንጋህንም ጋርድ ፡ አድነንም ተንከባከበን