፪ኛ ፡ የጴጥሮስ ፡ መልእክት - ምዕራፍ ፩ (1st Peter - Chapter 1)
| ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ። |
|
፩፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሐዋርያ ፡ ጴጥሮስ ፥ እግዚአብሔር ፡ አብ ፡ አስቀድሞ ፡ እንዳወቃቸው ፡ በመንፈስም ፡ እንደሚቀደሱ ፥ ይታዘዙና ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ደም ፡ ይረጩ ፡ ዘንድ ፡ ለተመረጡት ፡ በጳንጦስና ፡ በገላትያ ፡ በቀጰዶቅያም ፡ በእስያም ፡ በቢታንያም ፡ ለተበተኑ ፡ መጻተኞች ፤ ጸጋና ፡ ሰላም ፡ ይብዛላችሁ። ፪፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ከሙታን ፡ በመነሣቱ ፡ ለሕያው ፡ ተስፋና ፡ ለማይጠፋ ፥ እድፈትም ፡ ለሌለበት ፥ ለማያልፍም ፡ ርስት ፡ እንደ ፡ ምሕረቱ ፡ ብዛት ፡ ሁለተኛ ፡ የወለደን ፡ የጌታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ አምላክና ፡ አባት ፡ ይባረክ ፤ ይህም ፡ ርስት ፡ በመጨረሻው ፡ ዘመን ፡ ይገለጥ ፡ ዘንድ ፡ ለተዘጋጀ ፡ መዳን ፡ በእምነት ፡ በእግዚአብሔር ፡ ኃይል ፡ ለተጠበቃችሁ ፡ ለእናንተ ፡ በሰማይ ፡ ቀርቶላችኋል። ፫፡ በዚህም ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ ይላችኋል ፥ ነገር ፡ ግን ፡ በእሳት ፡ ምንም ፡ ቢፈተን ፡ ከሚጠፋው ፡ ወርቅ ፡ ይልቅ ፡ አብልጦ ፡ የሚከብር ፡ የተፈተነ ፡ እምነታችሁ ፥ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሲገለጥ ፥ ለምስጋናና ፡ ለክብር ፡ ለውዳሴም ፡ ይገኝ ፡ ዘንድ ፡ አሁን ፡ ለጥቂት ፡ ጊዜ ፡ ቢያስፈልግ ፡ በልዩ ፡ ልዩ ፡ ፈተና ፡ አዝናችኋል። ፬፡ እርሱንም ፡ ሳታዩት ፡ ትወዱታላችሁ ፤ አሁንም ፡ ምንም ፡ ባታዩት ፡ በእርሱ ፡ አምናችሁ ፥ የእምነታችሁን ፡ ፍፃሜ ፡ እርሱም ፡ የነፍሳችሁን ፡ መዳን ፡ እየተቀበላችሁ ፥ በማይነገርና ፡ ክብር ፡ በሞላበት ፡ ሐሤት ፡ ደስ ፡ ይላችኋል። ፭፡ ለእናንተም ፡ ስለሚሰጠው ፡ ጸጋ ፡ ትንቢት ፡ የተናገሩት ፡ ነቢያት ፡ ስለዚህ ፡ መዳን ፡ ተግተው ፡ እየፈለጉ ፡ መረመሩት ፤ ፮፡ በእነርሱም ፡ የነበረ ፡ የክርስቶስ ፡ መንፈስ ፥ ስለ ፡ ክርስቶስ ፡ መከራ ፡ ከእርሱም ፡ በኋላ ፡ ስለሚመጣው ፡ ክብር ፡ አስቀድሞ ፡ እየመሰከረ ፥ በምን ፡ ወይም ፡ እንዴት ፡ ባለ ፡ ዘመን ፡ እንዳመለከተ ፡ ይመረምሩ ፡ ነበር። ፯፡ ለእነርሱም ፡ ከሰማይ ፡ በተላከ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ወንጌልን ፡ የሰበኩላችሁ ፡ ሰዎች ፡ አሁን ፡ ባወሩላችሁ ፡ ነገር ፡ እናንተን ፡ እንጂ ፡ ራሳቸውን ፡ እንዳላገለገሉ ፡ ተገለጠላቸው ፤ ይህንም ፡ ነገር ፡ መላእክቱ ፡ ሊመለከቱ ፡ ይመኛሉ። ፰፡ ስለዚህ ፡ የልቡናችሁን ፡ ወገብ ፡ ታጥቃችሁና ፡ በመጠን ፡ ኖራችሁ ፥ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሲገለጥ ፡ የምታገኙትን ፡ ጸጋ ፡ ፈጽማችሁ ፡ ተስፋ ፡ አድርጉ። ፱፡ እንደሚታዘዙ ፡ ልጆች ፡ ባለማወቃችሁ ፡ አስቀድሞ ፡ የኖራችሁበትን ፡ ምኞት ፡ አትከተሉ። ፲፡ ዳሩ ፡ ግን። እኔ ፡ ቅዱስ ፡ ነኝና ፡ ቅዱሳን ፡ ሁኑ ፡ ተብሎ ፡ ስለ ፡ ተጻፈ ፡ የጠራችሁ ፡ ቅዱስ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ እናንተ ፡ ደግሞ ፡ በኑሮአችሁ ፡ ሁሉ ፡ ቅዱሳን ፡ ሁኑ። ፲፩፡ ለሰው ፡ ፊትም ፡ ሳያደላ ፡ በእያንዳንዱ ፡ ላይ ፡ እንደ ፡ ሥራው ፡ የሚፈርደውን ፡ አባት ፡ ብላችሁ ፡ ብትጠሩ ፡ በእንግድነታችሁ ፡ ዘመን ፡ በፍርሃት ፡ ኑሩ። ፲፪፡ ከአባቶቻችሁ ፡ ከወረሳችሁት ፡ ከከንቱ ፡ ኑሮአችሁ ፡ በሚያልፍ ፡ ነገር ፡ በብር ፡ ወይም ፡ በወርቅ ፡ ሳይሆን ፥ ነውርና ፡ እድፍ ፡ እንደ ፡ ሌለው ፡ እንደ ፡ በግ ፡ ደም ፡ በክቡር ፡ የክርስቶስ ፡ ደም ፡ እንደ ፡ ተዋጃችሁ ፡ ታውቃላችሁ። ፲፫፡ ዓለም ፡ ሳይፈጠር ፡ እንኳ ፡ አስቀድሞ ፡ ታወቀ ፥ ነገር ፡ ግን ፡ እምነታችሁና ፡ ተስፋችሁ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ይሆን ፡ ዘንድ ፥ ከሙታን ፡ ባስነሣው ፡ ክብርንም ፡ በሰጠው ፡ በእግዚአብሔር ፡ በእርሱ ፡ ስለምታምኑ ፡ ስለ ፡ እናንተ ፡ በዘመኑ ፡ መጨረሻ ፡ ተገለጠ። ፲፬፡ ለእውነት ፡ እየታዘዛችሁ ፡ ግብዝነት ፡ ለሌለበት ፡ ለወንድማማች ፡ መዋደደ ፡ ነፍሳችሁን ፡ አንጽታችሁ ፡ እርስ ፡ በርሳችሁ ፡ ከልባችሁ ፡ አጥብቃችሁ ፡ ተዋደዱ። ፲፭፡ ዳግመኛ ፡ የተወለዳችሁት ፡ ከሚጠፋ ፡ ዘር ፡ አይደለም ፥ በሕያውና ፡ ለዘላለም ፡ በሚኖር ፡ በእግዚአብሔር ፡ ቃል ፡ ከማይጠፋ ፡ ዘር ፡ ነው ፡ እንጂ። ፲፮፡ ሥጋ ፡ ሁሉ ፡ እንደ ፡ ሣር ፡ ክብሩም ፡ ሁሉ ፡ እንደ ፡ ሣር ፡ አበባ ፡ ነውና ፤ ሣሩ ፡ ይጠወልጋል ፡ አበባውም ፡ ይረግፋል ፤ ፲፯፡ የጌታ ፡ ቃል ፡ ግን ፡ ለዘላለም ፡ ይኖራል። በወንጌልም ፡ የተሰበከላችሁ ፡ ቃል ፡ ይህ ፡ ነው።
|