ደግነትህ (Degeneteh) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

፬
(4)

አልበም
(ውሳኔዬ)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፫ (2023)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 6:08
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

እኔን የሚረዳኝ የሚደግፈኝ
ደግሞ ሚያቆመኝ የሚያበረታኝ
ደግነትህ ነው ደግነትህ
ቸርነትህ ነው ቸርነትህ

ከተመስገን ሌላ ምን እላለሁ ሌላ
ምን እላለሁ ሌላ
ከተባረክ ሌላ ምን እላለሁ ሌላ
ምን እላለሁ ሌላ

እግዚአብሔር ሆይ ላንተ ምስጋና እሰዋለሁ
በዝማሬ ስምህን አወድሰዋለሁ
መግለፅ ስላቃታት የፍቅርህን ጥልቀት
ነፍሴን ከጨለማ ስታወጣት ድንገት

እንደገና አከብርሃለሁ እንደገና ሆሆ
እንደገና ሃሃ
እንደገና አመሰግናለሁ እንደገና ሆሆ

እኔን የሚረዳኝ የሚደግፈኝ
ደግሞ ሚያቆመኝ የሚያበረታኝ
ደግነትህ ነው ደግነትህ
ቸርነትህ ነው ቸርነትህ

ስለቸርነትህ ዘርዝሬ ላወሳ
የቱ ጋ ጀምሬ የቱ ጋላበቃ
ከውቂያኖስ ባህር ምህረትህ ይሰፋል
ቢወራ ቢነገር ከመታወቅ ያልፋል

እንደገና አከብርሃለሁ እንደገና ሆሆ
እንደገና ሃሃ
እንደገና አመሰግናለሁ እንደገና ሆሆ

እኔን የሚረዳኝ የሚደግፈኝ
ደግሞ ሚያቆመኝ የሚያበረታኝ
ደግነትህ ነው ደግነትህ
ቸርነትህ ነው ቸርነትህ

ከተመስገን ሌላ ምን እላለሁ ሌላ
ምን እላለሁ ሌላ
ከተባረክ ሌላ ምን እላለሁ ሌላ
ምን እላለሁ ሌላ

ይኸው ላንተ ምስጋናዬ
ይኸው ላንተ ዝማሬዬ
ሌላ ምሰጥህ የለምና አከብርሃለሁ እንደገና
ሌላ ምሰጥህ የለምና አከብርሃለሁ እንደገና

እንደገና አከብርሃለሁ እንደገና ሆሆ
እንደገና ሃሃ
እንደገና አመሰግናለሁ እንደገና ሆሆ