ምኔ ደስ አሰኝቶህ (Mene Des Asegntoh) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)


(Volume)

Bejemer Ayqerm
(Bejemer Ayqerm)

ቁጥር (Track):

፩ (1)

ርዝመት (Len.): 5:06
ጸሐፊ (Writer): አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw MeleseProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

ስርቅህ እየቀረብከኝ ስጠላህ እየወደድከኝ
ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2

ምስኪኑን ታናሽ ሰው ኧረ እንዴት ውደድከኝ
እንዳገለግልህ እኔን የመረጥከኝ
አሉ እኮ ጌታ ሆይ ከኔ የሚበልጡ
በሰው አይን የሞሉ ተመርጠው የኖሩ

ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2

ብዙዋች እያሉ ከኔ የተሻሉ
ብዙ ዝና ያላቸው አንቱ የተባሉ
ምኔ ደስ አሰኘህ እንዲ የወደድከኝ
እኔን ስትጠራ ወዳጅ ልትሆነኝ

ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2

ምንድን ነው ምኪያቱ እንዲ ለመውደድህ
በፀጋህ አንስተህ ምስኪኑን ማክበርህ
ሰው የረሳውን ሰው ልትቀባው መጥራትህ
እኔስ አስገረመኝ ጌታ አሰራርህ

ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2

መጀመሪያም መጨረሻዬ
እየሱስ ነው የኔ ምርጫዬ
ከሱ ሌላ አልመኝም
እንደ ጌታ ማንም አይሆነኝም

ሰው ያረገኝን ጌታ አልክደውም
ያደረገልኝን አልረሳውም
የጠራኝን ጌታ ጌታ አልክደውም
ያደረገልኝን አልረሳውም

ስርቅህ እየቀረብከኝ ስጠላህ እየወደድከኝ
ምኔ ደስ አሰኝቶህ ነው ከኔ ጋር ወዳጅ የሆንከው/2