አምላኬ (Amlake) - አስፋው ፡ መለሰ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
አስፋው ፡ መለሰ
(Asfaw Melese)

፲
(10)

Asfaw Melese
(Asfaw Melese)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፮ ((2005))
ቁጥር (Track):

፲ (10)

ርዝመት (Len.): 5:06
ጸሐፊ (Writer): ቃዴስ ሚዲያ Melkamu Tesfaye
(Kades media Melkamu TesfayeProperty "Writer" has a restricted application area and cannot be used as annotation property by a user.)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአስፋው ፡ መለሰ ፡ አልበሞች
(Albums by Asfaw Melese)

ዘማሪ አስፋው መለሰ
አምላኬ
ማነው ምሸከመን ሰብስቦ አሳዳጊ
የፍቅር ልብ ያለው የጠፋን ፈላጊ
አልባሽ አጣን እኮ እርቃንን የሚሸፍን
ማነው ለኛ ዛሬ አባት የሚሆን

ማነው ምሸከመን ሰብስቦ አሳዳጊ
የፍቅር ልብ ያለው የጠፋን ፈላጊ
አልባሽ አጣን እኮ እርቃንን የሚሸፍን
ማነው ለኛ ዛሬ አባት የሚሆን

አምላኬ ሰብስቤን አሳድገን እራራልን
ከአንተ ወዴት እንሄዳለን አንተው ነህ እያለህን
አምላኬ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን
ለኛ ማን ይሆናል
አባቴ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን
ለኔ ማን ይሆናል

የቱ ነው እረኛው መንጋውን ጠባቂ
ጠብቆ ሚያሳድግ ከአውሬ ከነጣቂ
ሰምቶ የሚያሰማን ስጠን ባለራዕይ
አይኖቹ የበሩ አጥርቶ የሚያይ

አምላኬ ሰብስቤን አሳድገን እራራልን
ከአንተ ወዴት እንሄዳለን አንተው ነህ እያለህን
አምላኬ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን
ለኛ ማን ይሆናል
አባቴ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን
ለኔ ማን ይሆናል

ነገር ጨላልሞበት ግራ ለተጋባው
ምድረበዳው ኑሮ ተስፋ ላሳጣው ሰው
አሩሩ በዝቶበት ለሚቅበዘበዘው
እግዚአብሄር እንዳንተ የሚያሳርፍ ማነው

አምላኬ ሰብስቤን አሳድገን እራራልን
ከአንተ ወዴት እንሄዳለን አንተው ነህ እያለህን
አምላኬ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን
ለኛ ማን ይሆናል
አባቴ እንዳንተ ማን ኧረ ማን ኧረ ማን
ለኔ ማን ይሆናል