ባንተ እጅ ነው (Bante Ej) - ቢንያም ፡ ዋለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale)

፫
(3)

አልበም
(ያይ ይናገር)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2017)
ቁጥር (Track):

፫ (3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢንያም ፡ ዋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Binyam Wale)

ሸክላ ሠሪ በእጁ ያለውን ጭቃ
እንደሚሠራው አድርጎ ጠቃሚ ዕቃ
በእጅህ ነው ያለው ጌታ የኔም ነገር
ይወድቃል ብዬ ልቤ አይሸበር

ባንተ እጅ ነው ባንተ እጅ ነው
ባንተ እጅ ነው ጌታ የሕይወቴ ዕጣ ፈንታ
ባንተ እጅ ነው ባንተ እጅ ነው
ባንተ እጅ ነው ጌታ የሕይወቴ ዕጣ ፈንታ

ባንተ እጅ ያለ አይበላሽም
ኢየሱስ የያዝከው አይበላሽም

ጊዜ አያልፍበትም የሰጡህ በአደራ
ይበላሻል ተብሎ ከቶ የማያስፈራ
ሕይወቴን በእጅህ ላይ አኖረዋለሁኝ
የማመልክህ አምላክ ታማኝ ነህ አውቃለሁ

ሕይወቴን አመንኩት አምላኬ እጅህ ላይ
ታማኝ ነህ ዘላለም በምንም አልሰጋም
ማን ጥሎ ያውቃል የፍቅር እጅህ
እኔ ምስክር ነኝ ልናገርልህ