ዕልልታ (Elilta) - ቢንያም ፡ ዋለ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search
ቢንያም ፡ ዋለ
(Binyam Wale)

፫
(3)

አልበም
(ያይ ይናገር)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፮ (2017)
ቁጥር (Track):

፭ (5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቢንያም ፡ ዋለ ፡ አልበሞች
(Albums by Binyam Wale)

ዕልልታ ሰው ላረገኝ ጌታ
ዕልልታ ጠላቴን ለመታ
ዕልልታ ሕያው ላረገኝ
ዕልልታ ከሞት ላዳነኝ

በእኔና ሞት መሃል ቀርቶ አንድ ስንዝር
ውድቀቴን ስጠብቅ በጭንቀት ሳጣጥር
ከአዳኙ አመለጥሁ እንደወፍ በርሬ
ለአዳኜ አበዛለሁ ምስጋና ዝማሬ

ዕልልታ ሰው ላረገኝ ጌታ
ዕልልታ ጠላቴን ለመታ
ዕልልታ ሕያው ላረገኝ
ዕልልታ ከሞት ላዳነኝ

ወጥመድ ተዘርግቶ በሞት ሸለቆ
ጠላት ሲጠብቅ ድብቅ ሽምቆ
አመለጥኩኝ ባንተ ነፍሴን ከሚሻ
ነጻ አወጣኸኝ ሆንከኝ መሸሻ

ምስጋና አምልኮ
ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ
አልጠገብኩም ዛሬም

ዕልልታ ሰው ላረገኝ ጌታ
ዕልልታ ጠላቴን ለመታ
ዕልልታ ሕያው ላረገኝ
ዕልልታ ከሞት ላዳነኝ

ስለ ስሙ መራኝ በጽድቅ መንገድ
ነፍሴንም አዳናት ከአዳኞች ወጥመድ
አልተሰናከልኩም ባልፍም በሞት ጥላ
እግዚአብሔር አምላኬ ሆኖልኝ ከለላ

ወጥመድ ተዘርግቶ በሞት ሸለቆ
ጠላት ሲጠብቅ ድብቅ ሽምቆ
አመለጥኩኝ ባንተ ነፍሴን ከሚሻ
ነጻ አወጣኸኝ ሆንከኝ መሸሻ

ምስጋና አምልኮ
ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ ጨምሬ
አልጠገብኩም ዛሬም