Yoseph Ayalew/Serayien Yeserahelegn/Tedegefiewalehu

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to navigation Jump to search

ዘማሪ ፡ ዮሴፍ ፡ አያሌው
አልበም ፡ ሥራዬን ፡ የሠራህልኝ


አሃሃ ፡ ለሚመኩበት ፡ አሃሃ ፡ ጋሻ ፡ ይሆናል
አሃሃ ፡ ተስፋ ፡ ላደረጉት ፡ አሃሃ ፡ መች ፡ ያሳፍራል (፪x)


መታመኛዬ ፡ ቸሩ ፡ ጌታዬ
ነገን ፡ አልፈራም ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ብዬ
ምን ፡ ይሆን ፡ ብዬ (፪x)


ደመናን ፡ አይቼ ፡ ይዘንባል ፡ አልልም
ጐተራዬ ፡ ሞልቷል ፡ ብዬ ፡ አልደገፍም (፪x)


መታመኛዬ ፡ ቸሩ ፡ ጌታዬ
ነገን ፡ አልፈራም ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ብዬ
ምን ፡ ይሆን ፡ ብዬ (፪x)


ተደግፌዋለሁ ፡ አሃሃ ፡ ታምኜበታለሁ ፡ ኦሆሆ (፬x)
ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ ኢየሱስ ፡ ይታመናል (፫x)


አይሸነጋጋልም ፡ እውነት ፡ ይናገራል
ያለውን ፡ ሊፈጽም ፡ በቃሉ ፡ ይተጋል (፪x)


መታመኛዬ ፡ ቸሩ ፡ ጌታዬ
ነገን ፡ አልፈራም ፡ ምን ፡ ይሆን ፡ ብዬ
ምን ፡ ይሆን ፡ ብዬ (፪x)


አሃሃ ፡ ሃሰትን ፡ አያውቅ ፡ አሃሃ ፡ ቃሉ ፡ እውነተኛ
አሃሃ ፡ ያለውን ፡ ሊያደረግ ፡ አሃሃ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)
ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ ኢየሱስ ፡ ይታመናል (፫x)


ተደግፌዋለሁ ፡ አሃሃ ፡ ታምኜበታለሁ ፡ ኦሆሆ (፬x)
ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ ኢየሱስ ፡ ይታመናል (፫x)


አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ ጌታ ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው
ዛሬም ፡ ሊሚጠሩት ፡ እርሱ ፡ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ነው (፪x)


የሚያኮራ ፡ ነው ፡ የሚያስተማምን
ጌታን ፡ የያዘ ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ ሊሆን ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ ሊሆን (፪x)


አሃሃ ፡ ዘለዓለም ፡ ነዋሪ
አሃሃ ፡ እርጅና ፡ አያውቀው
አሃሃ ፡ አልፋና ፡ ኦሜጋ
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x)


ይታመናል ፡ ጌታ ፡ ይታመናል
ይታመናል ፡ ኢየሱስ ፡ ይታመናል (፫x)